
“አረጀ ይሉኛል አወይ የሰው ነገር
መቸ ተወልዶ ያውቃል ነጭ እምቦሳ በሀገር”
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) መኖርም መሞትም በሀገር ሲሆን ያምራል በማለት በ81 ዓመታቸው አሸባሪውን
ትህነግ ለመፋለም ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ከአሁን በኋላ የማንም ባንዳ ተከዜን ተሻግሮ የወልቃይትን ምድር አይረግጥም
ብለዋል፡፡ ለሀገራቸው ብሎም ለአካባቢያቸው ሰላም ዘብ ሊቆሙ ለወረዳው የጸጥታ ቡድን አሳውቀው መለዮ ለብሰው መሣሪያ
አንግተው ወደ ተከዜ ጉዞ ላይ ናቸው- የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምሥራቅ በለሳ የኪብዛ ቀበሌ ነዋሪና የ81 ዓመት ታጋይ ማንአለው
በየነ፡፡
ታጋይ ማንአለው ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ ብዙ ጦርነቶችን፣ ክፉና ደግ ታሪኮችን አሳልፈዋል።
ደርግን ለመጣል በነበረው ትግል የአሸባሪው ትህነግን ክፉ የተንኮል ሴራ ሳላውቅ 80 መትረየስ ማርኬ አስረክቤ ነበር፤ አሁን
ግን ክፋትና ተንኮላቸውን አውቂያለሁ ያሉት ታጋይ ማንአለው አሁን ትህነግ ሀገሩንና ወገኑን የከዳ ባንዳ መሆኑን ተረድቻለሁ፤
ተወልደን ያደግንበትን ነግደን ያተረፍንበትን ወልቃይት ጠገዴን ለመቀማት የሚያደርገውን ከንቱ ቅጀት ለማክሸፍ ይኸው
ተሰልፊያለሁ” ብለዋል፡፡
የሀገር ሰላም ጉዳይ የሕጻን፣ የወጣት ፣ የሽማግሌ እና የአዛውንት ብቻ አይደለም የሚሉት አርበኛው “ጦርነት የጥበብ እንጂ
የጉልበትና የጉራ አይደለም” ነው ያሉት፡፡
ጥበብን፣ ጀግንነትንና ለሀገር መሞትን ደግሞ አርበኛ አባቶቻችን አውርሰውናል እሱን ደግሞ በተግባር ማሳየት አለብን ብለዋል።
ሀብትና ዝና ሁሉም ነገር አላፊና ጠፊ ነው የሚሉት ታጋዩ ታሪክ ግን በእውነትነቱ ጸንቶ ዘላለም ይኖራል፤ በመሆኑም ሁሉም ሰው
ለልጆችም እውነትን ፣ ለሀገር መሞትን ፣ የአባቶቻችንን የጀግንነት ታሪክ ማውረስ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ወጣቱ ትውልድ ስለ ሀገሩ ሰላምና ደኅንነት ሌት ተቀን መጨነቅ እንዳለበትም አስረድተዋል፡፡ የአባቶቹን ታሪክ የሚጠብቅ
ትውልድ ለውስጥም ኾነ ለውጭ ጠላት እንደ ኮሶ የመረረ በአንድነት ክንዱን ያበረታ መሆን እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡
መረጃው የተገኘው ከጠገዴ ወረዳ ኮምዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m