
ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ሁለት ወጣት ባለሀብቶች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር ለሚያከናውነው ማኅበራዊ ሥራ የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ።
ወጣት ማናዬ ሰንደቁ እና አደም ከድር የተሰኙ የሆራ እና ኤም ደብሊው ኤስ የተሰኘ ኩባንያ ባለቤቶች ናቸው የገንዘቡን ድጋፍ
ያደረጉት።
ከሁለቱም ባለሀብቶች የተገኘው 20 ሚሊዮን ብር ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ይውላል፡፡ 10 ሚሊዮን ብር ደግሞ የከተማ
አስተዳደሩ ለሚያከናውነው የምገባ መርኃግብር የሚውል ነው ተብሏል።
ባለሀብቶቹ በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የምገባ መርኃግብር በየዓመቱ የማያቋርጥ የ2 ሚሊዮን ብር እያበረከቱ መሆኑም
ተጠቅሷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለስጦታው ምስጋና አቅርበው የወጣት ባለሀብቶቹ በጎ ሥራ
ተደጋግፎ ሀገር ለማሳደግ ለሚደረገው ጉዞ ትልቅ አቅም ነው ብለዋል።
ምክትል ከንቲባዋ መንግሥት እና ባለሀብቱ በእንዲህ አይነት መልኩ ከተደጋገፉ የበርካቶች ህይወት ይሻሻላል ነው ያሉት፡፡
ሌሎችም ይህንን በጎ ሥራ በመቀላቀል ብዙዎችን ከወደቁበት ለማንሳት እንዲነሳሱ ጥሪ አቅርበዋል።
ወቅቱ ያለው ለሌለው እየረዳ ተያይዞ የሚያድግበት በመሆኑ ባደረግነው ሥራ የአዕምሮ እርካታ እናገኛለን ብለዋል ባለሀብቶቹ።
ባለሀብቶቹ ከዚህ በፊት በግንባር ለሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ፣ ለገበታ ለሀገር 40 ሚሊዮን፣ ለገበታ
ለሸገር 10 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ገላን ላይ አዳሪ ትምህርት ቤት እና እና ኮብል ስቶን መንገድ መገንባታቸውን በርክክብ ሥነ-
ሥርዓቱ ወቅት መገለጹን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m