በአሚሶም ሴክተር 6 የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት 5ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ የሜዳሊያ ሽልማት ተበረከተለት፡፡

219

በአሚሶም ሴክተር 6 የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት 5ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ የሜዳሊያ ሽልማት ተበረከተለት፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአሚሶም ሴክተር 6 የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት 5ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ
የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
በሽልማት መርኃግብሩ ላይ የጁባ ላንድ ምክትል ፕሬዝዳት መሐመድ ሰይድ እንዳሉት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል
አልሸባብን ለማስወገድ ያደረጋችሁት የግዳጅ አፈፃፀም ውጤታማ ነው ፤ ሠራዊቱ በዲስፕሊኑ የታነጸ ከሕዝቡ ጋር ጥሩ የሆነ
ግንኙነት ያለው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በአሚሶም ሴክተር 6 የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት 5ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ በአካባቢው አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ላሳየው
ቁርጠኝነት የሜዳሊያ ሽልማት በክብር መሰጠቱን ነው የተናገሩት፡፡
የሴክተር 6 አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል አበባው ሰይድ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል፣ የኬኒያና የሴራሊዮን የፖሊስ
ኃይል እንዲሁም የዩ ኤን አጋዥ ኃይሎች ዓመቱን ሙሉ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ ሰላም በማስከበር ረገድ ስመ ጥር ሃገር እንደሆነችና በተለይ በሶማሊያ የአልሸባብን ቡድን በማስወገድ
እንዲሁም የገንዘብ ምንጩን በማዳከም የሶማሊያን ሰላም በማጠናከር ትልቁን ሚና እየተወጣች ነው ብለዋል፡፡
የ5ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሰፋ መኮንን በተሰማራንበት የግዳጅ ቀጣና ከሀገሪቱ አስተዳደር፣ ከጸጥታ አካላትና
ከሕዝቡ ጋር በመቀናጀት አልሸባብን በጋራ በመዋጋት ኅብረተሰቡ ሰላሙ እንዲጠበቅ በርካታ ግዳጆችን ተወጥተናል ነው ያሉት፡፡
በቀጣይም ይህንን አጠናክረን እንቀጥላለን ማለታቸውን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ
ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበ2013/ 14 መኸር ዘመን 375 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እየተሠራ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
Next articleኢትዮ ቴሌኮም የላቀ የኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን የአራተኛው ትውልድ “የ4 ጂ ኤል ቲ ኢ አድቫንስድ” የኢንተርኔት አገልግሎት በሰሜን ሰሜን ምዕራብ ሪጅን አስጀመረ።