
በ2013/ 14 መኸር ዘመን 375 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እየተሠራ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ምርትና ምርታማነትን የሚጨምሩ ግብዓቶች የማሰራጨት ሥራ እየተጠናቀቀ መሆኑንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ኤክስቴንሽን ዳይሬክተር ጀኔራል አቶ ገርማሜ ጋሮማ
እንደገለጹት፤ የ2013/14 መኸር ዘመን 13 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በሰብል በመሸፈን 375 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አቅዶ እየሠራ ነው።
መረጃው እስከ ተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ለማረስ ከታቀደው መሬት መካከል 12 ሚሊዮን ሄክታር ታርሷል። እስከ አሁን ከታረሰው
መሬት ሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሄክታር መሬት ቅድሚያ በሚዘሩ እንደ በቆሎ፣ ማሽላ በመሳሰሉ ስብሎች ተሸፍኗል ብለዋል።
የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለመጨመር የሚያስችሉ ስልጠናዎች መሰጠቱን ጠቁመዋል፡፡ በተመሳሳይ ምርትና
ምርታማነት የሚጨምሩ የግብዓት አቅርቦት ሥርጭት ሥራም በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
የግብርና ግብዓት አቅርቦት ሥርጭት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር በአራት ሚሊዮን ኩንታል ብልጫ እንዳለው
ያስታወቁት አቶ ገርማሜ፤ 18 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ግዥ ተፈፅሟል። 15 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ወደብ ላይ ደርሶ 13
ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ኩንታል ወደ ማዕከላት መሰራጨቱን አመልክተዋል።
ወደብ ላይ ከደረሰ ማዳበሪያ 12 ሚሊዮን 785 ሺህ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ወደ እያንዳንዱ ቀበሌ ደርሷል። እነዚህም ከሰኔ 15
በፊት ሥርጭት ከስምንት ሚሊዮን ኩንታል በላይ አርሶ አደሮች እጅ ደርሷል ብለዋል።
ሥርጭቱ በክልሎች ደረጃ እስከ አሁን በተደረገው ሥርጭት በአማራ 76 ፣ ኦሮሚያ 80፣ ደቡብ ክልክ 80 ፣ ቤኒሻንጉል 87፣
ሲዳማ 67 ፣ ትግራይ 45 ፣ ግብርና ሥራ ኮርፖሬሽን 77 በመቶ ካቀዱት ዉስጥ በእጃቸው አስገብተዋል። የቀረውም በቅርቡ
ተሰራጭቶ እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል።
በክልሎች ፍላጎት መሰረት 392 ሺህ 423 ኩንታል ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሮች ተሰራጭቷል፤ የቀረው እስከ ሐምሌ አጋማሸ ድረስ
ሙሉ በሙሉ ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል፡፡
ከክልሎች በቀረበው ፍላጎት መሰረት የሚያስፈልገው ሀገራዊ የአግሮ ኬሚካል (ፀረ-አረምና ፀረ ተባይ) አንድ ሚሊዮን 692 ሺህ
313 ሊትር ግዥ ተፈፅሟል። ሀገር ውስጥ የማስገባት ሥራ እየተከናወነ ነው፤ አረም እስከሚደርስ ድረስ አርሶ አደሮች እጅ
የማድረስ ሥራ ይሠራል ብለዋል። ኢፕድ እንደዘገበው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m