የተለያዩ የአማራ ክልል የመንግሥት ተቋማት የሥራኃላፊዎችና ሠራተኞች በአማራ ሕዝብ ላይ ለሚቃጠው ጥቃት መልስ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ።

208

የተለያዩ የአማራ ክልል የመንግሥት ተቋማት የሥራኃላፊዎችና ሠራተኞች በአማራ ሕዝብ ላይ ለሚቃጠው ጥቃት መልስ
ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ።
የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞቹ ለህልውና የሕግ ማስከበር ዘመቻው የወር ደሞዛቸውንም ሰጥተዋል።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የመከሩት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አመራሮችና
ሠራተኞች ለህልውና ዘመቻው የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለመስጠት ወስነዋል። ሠራተኞቹ በዚህ ወቅት ገንዘባቸውን ብቻ ሳይሆን
የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ጥላሁን መሃሪ አስታውቀዋል።
የአማራ ክልል ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሠራተኞችም በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መክረዋል። ሠራተኞቹ ለነፃነታችን
እስከ ህይወት መስዋእትነት ለመክፍል ዝግጁ ነን ብለዋል።
ለህልውና ዘመቻውም በአንድ ዓመት የሚከፈል የአንድ ወር ደሞዛቸዉን መስጠት እንዲሁም ደም ለመለገስ እና የክልሉ
መንግሥት በሚያደርገው ጥሪ ሁሉ ለመሰለፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
የአማራ ክልል የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሠራተኞችም በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ከተወያዩ በኋላ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ
ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል።
የአንድ ወር ደሞዛቸውንም ከሐምሌ ወር ጀምሮ ለመስጠት ወስነዋል።
በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ የተወያዩት የአማራ ክልል መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሠራተኞች ደግሞ በአማራ ሕዝብ
ላይ የሚቃጣን ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት እስከ ህይወት መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ከሐምሌ ወር ጀምሮም ለህልውና ዘመቻው በአንድ ዓመት የሚቆረጥ የወር ደሞዝ ለመስጠትም ወስነዋል።
የምሥራቅ ጎጃም ዞን አጠቃላይ አመራሮችም ለወቅታዊ ተልዕኮ የወር ደሞዛቸውን በአንድ ዓመት ክፍያ መስጠታቸውን
አስታውቀዋል፡፡
መረጃው ከየተቋማቱ የተገኘ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ ከመቼውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ በተቀናጀ መንገድ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል” ዶክተር አረጋዊ በርሔ
Next articleበ2013/ 14 መኸር ዘመን 375 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ እየተሠራ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።