
“ኢትዮጵያ በአየር ንብር ለውጥ የኀብረተሰቡን የመቋቋም አቅም ለማሻሻል እርምጃዎችን እየወሰደች ነው” ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአየር ንብረት ለውጥ ከየትኛውም ሀገራት በበለጠ የሚጎዳው ታዳጊ ሀገሮችን በመሆኑ የዘመኑ ዋነኛ ተግዳሮት ሆኗል ሲሉ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ።
ፕሬዝዳንቷ ይሄን ያሉት በባንግላዴሽ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመከላከል የሚያስፈልገዉን ገንዘብ ለማሰባሰብ በተዘጋጀ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
ኢትዮጵያ ተጋላጭ እንደመሆኗ መጠን በተለያዩ የጋራ እና ብሔራዊ እንቅስቃሴዎች አማካኝነት የህብረተሰቡን የመቋቋም አቅም ለማሻሻል እርምጃዎችን እየወሰደች መሆኑን ገልጸዋል።
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ያባባሰ ሲሆን ሁለቱም የተቀናጀ እና ፈጣን የጋራ እርምጃን እንደሚጠይቁም ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ያደጉ ሀገራትም ይህንን ችግር ለመቅረፍ የድርሻቸውን ፍጥነት እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውንም ከኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m