
“የሕዳሴው ግድብ በቀጣናው የጋራ ብልጽግናን ለማምጣት ያስችላል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር)
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በታላቁ የህዳሴ ግድብ ሙሌት ምክንያት በሱዳንና በግብጽ ሕዝቦች ላይ የሚደርስ ምንም ዓይነት ጉዳት እንደሌለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡
ግድቡ ለሶስቱ ሀገራት የትብብር እንጂ የጠብ መንስዔ ሊሆን አይገባም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ በአረብኛ ቋንቋ ባሰፈሩት መልዕክት፡፡
የግድቡ ሙሌት በሚካሄድበት ወቅት ከውኃው ፍሰት ወደ ግድቡ የሚቀር ውኃ ካለም ጥቂት በመሆኑ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ የሚደርሰ ጉዳት አይኖርም ብለዋል፡፡
የግድቡ መገንባት በተለይ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በክረምት ወቅት የሚከሰትን የጎርፍ አደጋ በመከላከል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ገልጸዋል፡፡
ለአብነትም የህዳሴ ግድብ መገንባት የተረጋጋ የውኃ ፍሰት እንዲኖር በማድረግ በሱዳን ሮዘሪስ ግድብ አካባቢ የሚኖሩ ማኅበረሰቦችን የጎርፍ አደጋ ስጋት ይቀንሳል ብለዋል፡፡
የትብብር ምንጭ ተደርጎ ከተወሰደ ግድቡ በቀጠናው የጋራ ብልጽግናን ለማምጣት እንደሚያግዝ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m