“ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሁለት ሀገራት የሚኖሩ አንድ ሕዝቦች ናቸው” የኬንያ ምክትል ፕሬዚደንት

111

“ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሁለት ሀገራት የሚኖሩ አንድ ሕዝቦች ናቸው” የኬንያ ምክትል ፕሬዚደንት

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኬንያው ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሁለት ሀገራት የሚኖሩ አንድ ሕዝቦች መሆናቸውን ተናግረዋል።

በኬንያ የኢፌዴሪ አምባሳደር መለስ ዓለም ከምክትል ፕሬዚደንቱ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በዚሁ ወቅት በኢትዮጵያ የሚገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ኬንያን ጨምሮ ለቀጠናው ሀገራት ፋይዳው የጎላ መሆኑንም ገልጸዋል።

በግድቡ ላይ የሚካሄደውን የሶስትዮሽ ድርድር አስመልክተውም በኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን መካከል ያሉ አለመግባባቶች በአፍሪካዊ መፍትሔ ለአፍሪካዊ ችግሮች መርህ በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት በሚካሄደው የሶስትዮሽ ደርድር ማዕቀፍ መፍትሔ ሊያገኝ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ የተካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታም ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት አስተላልፈዋል።

አምባሳደር መለስ በበኩላቸው ኬንያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነቷ ላበረከተችው አስተዋፅኦ እና ላሳያችው አጋርነት ለኬንያ ሕዝብና መንግሥት ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የኢትዮጵያውያን የዘመናት ህልም መሆኑን ጠቅሰው፣ ጠቀሜታው ግን ለሁሉም መሆኑን አምባሳደር መለስ ለምክትል ፕሬዚደንቱ አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር ያላትን ፈርጀ-ብዙ ወዳጅነትና አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር እንደምትሠራም ገልጸዋል። መረጃው የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ነው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየጎርፍ አደጋን ለመቀነስ የተከናወኑ ተግባራት በአደጋው የሚፈጠር መፈናቀልን ከ80 እስከ 90 በመቶ እንደሚቀንሱ ተገለጸ፡፡
Next article“የሕዳሴው ግድብ በቀጣናው የጋራ ብልጽግናን ለማምጣት ያስችላል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር)