
የ6ኛ ሠርዶ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ለወልዲያ እና ለቆቦ ማኅበረሰብ ምስጋና አቀረበ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ)የ6ኛ ሠርዶ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ያሲን መሐመድ የወልዲያ እና የቆቦ ማኅበረሰብ ሠራዊቱ ለሕግ ማስከበር በተንቀሳቀሰበት ወቅትና ከዘመቻው በድል ሲመለስ ላደረገለት አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በሰሜን ዕዝ ሠራዊት ላይ የፈፀመውን የግፍ በትር ለመቀልበስ መከላከያ ሠራዊት ወደ ሰሜኑ ክፍል ሲንቀሳቀስ የወልዲያና የቆቦ ሕዝብ ውኃ እና ምግብ ይዞ በድል ተመለሱልን ልጆቼ ብሎ ሸኝቷቸው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡




“እኛም የሕዝብ ልጆቹ የጁንታው ቡድን በገባበት ሸርጥና ገደል እየገባን የአሸባሪ ቡድኑ አባላትን በመደምሰስና በመማረክ ለሕዝባችን የሚጠብቀውን ድል አስመዝግበናል” ነው ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል ያሲን ።
አሁን ላይ መንግሥት ሠራዊቱ የሕግ ማስከበሩን ዘመቻ በማጠናቀቁ ከሰሜኑ ክፍል እንዲወጣ በወሰነው መሠረት በሰላም ወደ ደጀን ሕዝባችን ገብተናል ብለዋል ፡፡
“ወደ ወልዲያ እና ቆቦ አካባቢዎች ስንገባ ልጆቼ በሠላም መጣችሁ ብሎ ያሳየውን ድጋፍ በእኔ እና በክፍለጦሩ ስም እያመሰገንኩ ቀጣይም መንግሥትና ሕዝብ የሚሰጠንን ማንኛውም ግዳጅ በድል ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን ለማረጋገጥ እወዳለሁ” ብለዋል ብርጋዴር ጀነራሉ።
የመረጃ ምንጭ፡- የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ