በመዲናዋ የሚኖሩ ባለሀብቶች ለመከላከያ ሠራዊትና ለህዳሴ ግድብ የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንደሚያበረክቱ አስታወቁ።

122
በመዲናዋ የሚኖሩ ባለሀብቶች ለመከላከያ ሠራዊትና ለህዳሴ ግድብ የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንደሚያበረክቱ አስታወቁ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ የሚኖሩ ባለሀብቶች ለኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊትና ለህዳሴ ግድብ የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንደሚያበረክቱ አስታወቁ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከባለሀብቶች ጋር በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ያዘጋጀው የውይይት መድረክ በሸራተን አዲስ አየተካሄደ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተና ጄነራል ባጫ ደበሌ ተገኝተዋል፡፡
በዚህ የውይይት መድረክ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ መከላከያ ሠራዊት ትግራይን ለቆ የወጣው በፖለቲካ ውሳኔ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በትግራይ የተበላሸው መሰረተ ልማት እንዲጠገን ህዝቡም ወደ ልማቱ እንዲመለስ በማሰብ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
ሌተና ጄነራል ባጫ ደበሌ በበኩላቸው ሠራዊቱ ትግራይን ለቆ ሊወጣ የነበረው እነ ስብሀት ነጋ በተያዙበት ወቅት ነበር በኋላ ግን ጊዜያዊ አስተዳደሩን ለማገዝ ይቆይ ተባለ ብለዋል፡፡
ህዝቡ በአራቱም አቅጣጫዎች ከሠራዊቱ ጋር እንዲዋጋ በማድረግ መንግስትን በዘር ማጥፋት ወንጀል ለመክሰስ በማሰብ ወያኔ በቅርቡ ያደረገውን እንቅስቃሴ በጥንቃቄ በመመልከት ህዝቡ ወደ ልቡ እንዲመለስ እድል ለመስጠት በማሰብ ትግራይን ለቀናል ብለዋል ጄነራሉ፡፡
ምንም እንኳን ጦሩ ለስትራቴጂ ከትግራይ ቢወጣም በክልሉ ዙሪያ በተጠንቀቅ ነው ያለው ብለዋል ጀነራሉ፡፡
አትጠራጠሩ የመከላከያ ሠራዊት በፈለገው ሰዓት መቀሌ ገብቶ ይወጣል ብለዋል፡፡
ባለሀብቶቹም ለሠራዊቱ እና ለህዳሴ ግድቡ የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንደሚያበረክቱ አስታውቀዋል፡፡
ለተሰው የሠራዊት አባላት ቤተሰቦችም ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡
ባለሀብቱ የሚያበረክተው ድጋፍ በውይይቱ ማጠቃለያ ይታወቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢቢሲ ዘግቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleፓን አፍሪካኒዝም በትዊተር ዘመቻው
Next article“የጸጥታው ምክር ቤት የህዳሴ ግድብ ጉዳይ በአፍሪካ ሕብረት ይታይ ማለቱ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት ነው” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ