
ከ250 ዓመታት በፊት የታተመ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ ለባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ተበረከተ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኪንግ ጀምስ ቅጂ በመባል በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚታወቀው ቀደምት ሙሉ የእንግሊዘኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ ምንጮች አንዱ የሆነው የ1769 እ.አ.አ የታተመው መጸሐፍ ቅዱስ ከአቶ ሳምሶን መኮንን ጣሰው ቤተሰብ ለቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን ተበርክቷል።
በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዶክተር ሒሩት ካሳው ፣ የባሕል ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ብዙነሽ መሰረት እና የቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሙሉጌታ ፍስሐ መገኘታቸውን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የማኅበራዊ ትስሰር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ