
“የጸጥታው ምክር ቤት የህዳሴውን ግድብ ጉዳይ የማየት ስልጣን የለውም” ኢንጅነር ስለሺ በቀለ
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 01/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያዊያን የሰዓት አቆጣጠር በዕለተ ሐምስ ከሌሊቱ 6:00 በዋሽንግተን ዲሲ
የሰዓት አቆጣጠር ደግም ከቀኑ አጋማሽ ላይ የጸጥታው ምክርቤት የዓለምን ትኩረት በሳበ አንድ ብርቱ ጉዳይ ላይ ሊመክር ሰዓት
ቆርጧል።
በተቆረጠው ሰዓት በኒው ዮርክ የተጀመረው የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባም በኢትዮጵያዊያን ተቃውሞ የታጀበ ነበር።
በሀገራቸው ጉዳይ ላይ የማይደራደሩት ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ወደ ኒው ዮርክ
በመትመም በጸጥታው ምክር ቤት ዋና መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት በመሰባሰብ ድርጊቱን በብርቱው አወገዙ።
“ግድቡ የእኔ ነው፤ የአፍሪካዊያን ችግር መፍትሔ የሚያገኘው በአፍሪካ ነው፤ የጸጥታው ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ላይ እጁን ያንሳ፤
የውጭ ጣልቃ ገብነት ይቁም… የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን በእልህና በፍጹም ሀገር ወዳድነት ስሜት አስተጋቡ።
የኢትዮጵያን ታላቁ ህዳሴ ግድብ የሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት መነሻ በማድረግ በቱኒዚያ በኩል የግብጽና የሱዳን ጥያቄ የቀረበለት
የጸጥታው ምክር ቤት የስብሰባውን ዓለማ ይፋ አድርጎ የምክር ቤቱ አባል ሀገራት ተወካዮች ሀሳባቸውን መስጠት ቀጠሉ።
የኬኒያ ተወካይ የአፍሪካውያን የጋራ እድገት ፍላጎት መገለጫ የሆነውን አጀንዳ 2063 መነሻ በማድረግ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ
በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት የጀመሩትን ድርድር ሊቀጥሉ እንደሚገባ የሀገራቸውን አቋም ገለጹ።
ተወካዩ ቀጠሉ “ጉዳዩ የአፍሪካ ጉዳይ በመሆኑ በጸጥታው ምክር ቤት የሚካሄድ ውይይት ውጤት አያመጣም፤ እናም ወደ አፍሪካ
ህብረት መመለስ አለበት” በማለት ጠንከር ያለ አስተያየታቸውን አስቀመጡ።
ሩሲያ ቀጠለች የህዳሴ ግድቡን ሂደት በቅርበት እየተከታተለች እንደምትገኝና የግድቡ ጉዳይ መፍትሔ ማግኘት ያለበት በአፍሪካ
ሕብረት ሊሆን እንደሚገባ አስገነዘበች።
ከሦስቱም ሀገራት ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዳላት የገለችው ቻይና በበኩሏ ጉዳዩ አፍሪካዊ መፍትሔ እንደሚያሻው አስረዳች።
እንግሊዝ በአፍሪካ ሕብረት አሸማጋይነት እየተካሄደ ያለው ድርድር ውጤታማ እንዲሆን ድጋፍ እንደምታደርግ ስትገልጽ፤ ፈረንሳይ
በበኩሏ በአፍሪካ ሕብረት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፊሊክስ ቺሴሼክዲ መሪነት
እየተካሄደ ያለው የሦስቱ ሀገራት ድርድር ጥረት መቀጠል እንደሚገባው አቋሟን አስታወቀች።
የኖርዎይ፣ ኒጀር፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ቬትናም እና ሌሎችም ሀገራት ተወካዮች ድርድሩ በአፍሪካ ህብረት ይካሄድ የሚል ሀሳባቸውን
ሰነዘሩ።
ጉዳዩን ገፍተው በድጋሜ ወደ ጸጥታው ምክር ቤት ያመጡት ግብጽና ሱዳንም ሀሳባቸውን ቀጠሉ። የአፍሪካ ህብረት ድርድር
በፍጥነት እየተካሄደ ባለመሆኑ፣ በተለይ የግድቡ የሁለተኛ የውኃ ሙሌት መጀመሩ በሕልውናችን ላይ አደጋ በመፍጠሩና አስቸኳይ
መፍትሔ ስለሚሻ፣ ጉዳዩም ፖለቲካ በመሆኑ የጸጥታው ምክር ቤት ይዳኘን የሚል የተለመደ ተማጽኗቸውን አቀረቡ።
በኢትዮጵያዊያን ተቃውሞ የታጀበው የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ዕድል ለኢትዮጵያ መስጠት ግድ ሆነበት።
በሕዳሴው ግድብ ጥልቅ ዕውቀት እንዳላቸው የሚነገርላቸው የኢትዮጵያ የውኃ ሙስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር
ስለሺ በቀለ “የጸጥታው ምክርቤት የተቋቋመው የጸጥታ ጉዳዮችን ሊያይ እንጅ የልማት ፕሮጀክት አጀንዳ ለማድረግ ባለመሆኑ
አጀንዳው ውድቅ ሆኖ ወደ አፍሪካ ህብረት መመለስ አለበት” በማለት ለግብጽና ሱዳን የራስ ምታት ለኢትዮጵያ አጋሮች ደግም
ኩራት የሆነ ንግግር አደረጉ።
ሚኒስትሩ የዓባይ ግድብ ጉዳይ ግብጽና ሱዳንን ስለሚጎዳ ሳይሆን በዋናነት ግብጽ በቅርቡ ደግሞ ሱዳን ግድቡን የማይደግፉት
በቅኝ ግዛት እሳቤ ራሳቸውን በመሸበባቸው ነው፤ ይህ ደ%8