
ኢትዮጵያውያን የጸጥታው ምክር ቤት በሕዳሴ ግድቡ ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ግብነት በመቃወም ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
የጸጥታው ምክር ቤት ግብጽና ሱዳን ባቀረቡት ጥያቄ አማካኝነት በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ስብሰባ ያደርጋል።
ምክርቤቱ የሚያካሂደውን ስብሰባ በመቃወም በአሜሪካ በተለያዩ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ኒው ዮርክ በሚገኘው የተመድ መሥሪያ ቤት ተገኝተው ሰልፍ እያካሄዱ ነው።