
በሰሜን ዕዝ የ6ኛ ሠርዶ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር የአየር መቃወሚያ ሻለቃ በሕግ ማስከበሩ ሂደት ስኬታማ ግዳጅ መፈጸሙ ተገለጸ።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 01/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ዕዝ የ6ኛ ሠርዶ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር የአየር መቃወሚያ ሻለቃ በሕግ ማስከበሩ ዘመቻ ስኬታማ ግዳጅ እንደፈጸመ ዋና አዛዥ ሻለቃ ጋሻው በቀለ ገልጸዋል።
ሻለቃ ጋሻው ያረምንለት፣ ያጨድንለት፣ ትምህርት ቤት የሰራንለት ሕዝብ ሲክደን አንድም ቀን ምንም ነገር ያላደረግንለት ኅብረተሰብ በየመንገዱ ውኃ እና ምግብ እያበላና እያጠጣ ለሠራዊታችን ያደረገው አቀባበል የተለየ ነበር ብለዋል፡፡
ለቀጣይም ሕዝብና መንግሥት የሚሰጣቸውን ግዳጅ የበለጠ ለመወጣት ትልቅ የሞራል ስንቅ እንደሆናቸው መናገራቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የ2ተኛ ሻምበል አዛዥ ም/መ/አ ፍርዱ ገረመው “መንግሥት እንድንወጣ ካደረገ በኋላ በምንወጣበት ጊዜ አጥፊው ሕዝቡን አስገድዶ እንዲሁም ጦርነቱን መልኩን ቀይሮ ቢመጣም ሠራዊታችን በጥንቃቄ አንድም ሕዝብ ሳይመታ በተመረጡ ዒላማዎች ላይ ብቻ በመተኮስ ሕዝባዊነቱን ጠብቆ ራሱ ጭምር እየተመታ የነበረውን ደፈጣ በጀግንነት ማስወገድ ችሏል” ብለዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ