በሲውዘርላንድ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዢ እየተፈጸመ ነው።

145
በሲውዘርላንድ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዢ እየተፈጸመ ነው።
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 01/2013 ዓ.ም (አሚኮ) መቀመጫውን ሲውዘርላንድ ያደረገው “እኔም ለወገኔ” ማኅበር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በከፍተኛ ገንዘብ የቦንድ ግዢ እየተፈጸመ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
ከ200 በላይ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያንን ያቀፈው ማኅበሩ፣ ከተለያዩ ሀገራት ኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ያልተገባ ጫና በጽኑ በመቃወም ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡
ከውጭም ከውስጥም ያሉ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ሉዓላዊነት እና ለራሳቸው ህልውና ጭምር በጋራ ሊቆሙ እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡
በሲውዘርላንድ የሚኖሩና እኔም ለወገኔ በተሰኘ ማኅበር የሚንቀሳቀሱ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድቡ የቦንድ ግዢ በመፈጸም ጫናውን ለመቋቋም የራሳቸውን አሻራ እያሳረፉ ነው፡፡
ህዳሴ ግድቡ ጉዳይ የህልውና ጉዳይ ነው በዚህ ሰዓት መከፋፈልን ወደ ጎን በመተው ከውስጥም ከውጭም በጋራ መረባረብ አለብን ብለዋል፡፡
“ለሀገራቸው ታላቅ ተጋድሎ የሚያደርጉ ዲያስፖራዎች እንዳሉ ሁሉ ለእኩይ ዓላማ የተሰለፉ ዲያስፖራዎች መኖራቸው ቢታወቅም ለመልካም ሥራ የተሰለፍን ግን ቁጥራችን ብዙ ነው” ብለዋል፡፡
ማህበሩ በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም የዘገበው ዋልታ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleለምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) ዋንጫ ውድድር በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ፡፡
Next articleበሰሜን ዕዝ የ6ኛ ሠርዶ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር የአየር መቃወሚያ ሻለቃ በሕግ ማስከበሩ ሂደት ስኬታማ ግዳጅ መፈጸሙ ተገለጸ።