“በምግብ ዋስትና ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የሚቀሩ ተማሪዎችን ቁጥር ለመቀነስ በትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ መርኃግብር ተግባራዊ መደረጉ አስፈላጊ ነዉ” የትምህር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ

354
“በምግብ ዋስትና ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የሚቀሩ ተማሪዎችን ቁጥር ለመቀነስ በትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ መርኃግብር ተግባራዊ መደረጉ አስፈላጊ ነዉ” የትምህር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 01/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ ፖሊሲ ማስፈጸሚያ ስትራቴጅ የማስጀመሪያ መርኃግብሩን እያከናወነ ይገኛል።
በመርኃግብሩ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ በትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ ተግባራዊ መደረጉ በምግብ ዋስትና ችግር ምክንያት ከትምህርት ቤት የሚቀሩ ተማሪዎችን ቁጥር ይቀንሳል ብለዋል።
እስካሁን በአዲስ አበባ ተግባራዊ ሲደረግ የነበረዉን የተማሪዎች ምገባ ክልሎችም ተግባራዊ ማድረግ ይኖርባቸዋል ነው ያሉት። የተማሪዎች ምገባ መርኃ ግብር ማስፈጸሚያ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ተግባራዊ እንዲኾን የክልል የሥራ ኀላፊዎች ትኩረት ሰጥተዉ ሊሠሩ ይገባል ተብሏል።
ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን በመላ ሀገሪቱ በትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባን ተግባራዊ ለማድረግ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራም ነው የተናገሩት፡፡
ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸዉ ላይ ተገኝተዉ ትምህርታቸዉን በተገቢዉ መንገድ እንዲከታተሉ እና ውጤታማ እንዲኾኑ ለማድረግ የተማሪዎች ምገባ መርኃ ግብር አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑም ተገልጿል።
ዘጋቢ፡- ኤልሳ ግኡሽ- ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article”ደጀን ወደ ሆነው ሕዝባችን ስንገባ የተደረገልን አቀባበል ሠራዊቱን ያስደመመ ነው” ኮሎኔል ሻምበል በየነ የ23ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ
Next article“ኢትዮጵያውያን ሁለተኛውን ዙር የሕዳሴ ግድብን ሙሌትና ሉዓላዊነታችንን ለማስጠበቅ፣ አንድና ብዙ ሆነን እንነሣ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)