
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት የምትሰጠው ችግኝ ቀጠናዊ ትብብርን የሚያጠናክር መሆኑን የአካባቢ
የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ገለጸ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር “ኢትዮጵያን እናልብሳት” በሚል መሪ ሃሳብ
በአገር አቀፍ ደረጃ 6 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡
አንድ ቢሊየን ችግኝ ደግሞ ለጎረቤት አገራት የሚሰጥ ሲሆን በዚህም ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ኬንያ
ለመድረስ የታቀደ መሆኑም ይታወቃል።
የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን ዛሬ በሱባ መናገሻ ደን አካባቢ የችግኝ ተከላ
አካሂዷል።
በዚሁ ወቅት ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፈቃዱ በየነ እንዳሉት፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአካባቢ ብክለትና የአየር ንብረት ለውጥ
የሚያስከትላቸውን ችግሮች በመፍታት ረገድ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል።
ለግብርና፣ ለበቂ ውሃ አቅርቦት፣ ለብዝሃ ህይወት ልማትና ጥበቃ፣ ለስነ ምህዳር አገልግሎት፣ ለስራ እድል ፈጠራ፣ ለደን
ውጤቶችና ለሌሎችም የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለጎረቤት አገራት የምታደርሰው ችግኝም ለቀጠናዊ ትብብር፣ ለልማት፣ በጋራ
ለማደግ እና የጋራ መድረክ ለመፍጠር የራሱ አስተዋጽኦ አለው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የጎረቤት ሀገራትን ትብብር የሚያጎለብት እና በሰላም አብሮ የመስራትን እድል የሚያጠናክር ነው ብለዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m