
የአማራ ክልል የጸጥታ ኀይል ሕዝብን ደጀን አድርጐ ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት በተጠንቀቅ ቆሟል፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ ሕዝብን ደጀን አድርገው በከወኑት የሕግ ማስከበር ዘመቻ ከፍተኛ ድል ማስመዝገባቸው ይታወሳል።
አሸባሪው ትህነግ አሁንም በአማራ ሕዝብ ላይ “የማወራርደው ሂሳብ አለኝ” በሚል የእብሪት ፉከራውን በአደባባይ ገልጿል።
ይህን የእብሪት ፉከራ ለመመከት የአማራ ክልል የጸጥታ ኀይል ሕዝብን አስተማማኝ ደጀን አድርጐ ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት በተጠንቀቅ ቆሟል።
የአማራ ልዩ ኀይል እና የአማራ ሚሊሻ ሕዝብን ደጀን አድርገው ያስመዘገቡትን ድል አጠናክረው እንደሚቀጥሉም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
የአማራ ሕዝብ ልዩ ኀይሉን ለማጠናከርና ደጀን ለመኾን እያደረገ ያለውን ተነሳሽነት ለማበረታታት የአማራ ፖሊስ የማርች ባንድ አባላትም በባሕርዳር ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ትርዒት ማሳየቱን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ