
በደሴ ከተማ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ ተጀመረ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ከተማ የተጀመረዉ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት 77 ሺህ የሚሆኑ በጎ
ፈቃደኞችን ተሳታፊ የሚያደርግ ነው። 57 ሚሊዮን ብር ወጭ እንደሚሸፍን ተገልጿል፡፡ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቱንም
የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አበበ ገብረ መስቀል የአቅመ ዳካሞችን ቤት በማደስ አስጀምረዋል።
የደሴ ከተማ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ ወይዘሮ ፈንታዬ ጋሻዉ በዚህ ክረምት ወቅት 18 የአቅመ ደካሞችን
ቤት ለማደስ
መዘጋጀታቸዉን ገልጸዋል። በበጎ ፈቃድ ሥራዉ ላይም በጎ ፈቃደኞች በንቃት ሊሳተፉ ይገባል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኀላፊ አባይነህ መላኩ እንዳሉት የሀገርን ዳር ድንበር ከማስከበር
ጀምሮ በግብርናው፣ በጤናውና በሌሎች ዘርፎችም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
ወጣቶች የአካባቢዉን ሰላም ለማስጠበቅ የራሱን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
የደሴ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሞላ ሁሴን በበኩላቸው የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር ወደ ግንባር
ለሄዱ የመከላከያ፣ የልዩ ኀይል እና የሚሊሻ ቤተሰቦችን መጠየቅ፣ መደገፍ እና ተገቢዉን እገዛ ማድረግ ከበጎፍቃደኞች
እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።
ከአቅመ ደካሞችን ቤት እድሳት መስጀመር ባለፈ የደሴ ከተማ የ2013 ዓ.ም የበጋ በጎ ፍቃድ አገልግሎት አፈፃፀም እና የ2013
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎች ላይ ምክክር ተደርጓል። በዕለቱ በበጋ ወቅት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና
ድርጅቶች እዉቅና ተሰጥቷል፡፡
ዘጋቢ:— ማሕሌት ተፈራ–ከደሴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m