
“የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ምርታማነትን ማሳደግና ለማምረቻው ዘርፍ ግብዓት እንዲሆን ለማድረግ መንግሥት
እየሠራ ይገኛል” ዶክተር አሕመዲን መሐመድ
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የዲጂታል ኢትዮጵያ የበይነ መረብ ውይይት አካል የሆነውና የግብርናውን ዘርፍ
በቴክኖሎጂ መደግፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ የበይነ መረብ ውይይት ተካሂዷል፡፡
ኢትዮጵያ የግብርና ዘርፏን ለማዘመንና የግብርና ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ ለማሳደግ እየሠራች
ትገኛለች፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር) የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ምርታማነትን
ማሳደግና ለማምረቻው ዘርፍ ግብዓት እንዲሆን ማድረግ ላይ መንግሥት በትኩረት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በሚደረገው ጥረት የዘርፉ ባለሙያዎች ትብብር ወሳኝ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው
የአርሶ አደሮችን ህይወት ለማሻሻልና ግብርናው እንዲዘምን ለማድረግ የዲጂታል ግብርና ፕላትፎርም መገንባትና የግብርና
ቴክኖሎጂ ሥራ ፈጠራ ላይ የተሰማሩትን መደገፍ እና ማበረታታት ላይ እንደሚሠራ መግለጻቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ
ሚኒስቴር የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
‹‹ለርሻ›› የተባለ የግብርና መረጃ መሥራችና ዋና ዳይሬክተር አቶ አብረሃም እንድሪስ ለአርሶ አደሮች በአጭር የስልክ ቁጥር ጥሪ
መረጃዎችን በተለያዩ የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች እየሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ያሏትን በርካታ የግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን አቅም በመጠቀም የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት ላይ
መሥራት እንደሚገባም ተጠቁሟል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን፣ የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማሳደግና መረጃ እንዲያገኙ ለማድረግ
ሰለሚሰጧቸው አገልግሎት፣ በዘርፉ ስላሉ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m