ከምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል አባል ሀገራት የተውጣጡ ወጣቶች በእንጦጦ ፓርክ ችግኝ ተከሉ።

122

ከምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል አባል ሀገራት የተውጣጡ ወጣቶች በእንጦጦ ፓርክ ችግኝ ተከሉ።
ባሕር ዳር: ሰኔ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ከምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኀይል አባል ሀገራት የተውጣጡ ወጣቶች በእንጦጦ
ፓርክ ችግኝ ተከሉ።
በምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል አዘጋጅነት የአባል ሀገራቱ ወጣቶች በሰላም ላይ ያተኮረ ልምድ ልውውጥና ችግኝ ተከላ
መርኃግብር ተካሂዷል።
ወጣቶቹ በቀጣናው ሰላምና ወቅታዊ ሁኔታ የወጣቶች ሚና ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።
ወጣቶቹ ዛሬ በእንጦጦ ፓርክ ችግኝ ተክለዋል። የተጠባባቂ ኃይሉን ዳይሬከተር ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎችም
ተገኝተዋል።
የተጠባባቂ ኀይሉ ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል ጌታቸው ሽፈራው “የአረንጓዴ ዐሻራ በማሳረፋችን ኮርተናል” ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥትም የተጠባባቂ ኀይሉ አባል ሀገራት ወጣቶች የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴ አካል እንዲሆኑ በመፍቀዱ
ይመሰገናል ነው ያሉት።
የአረንጓዴ ዐሻራ ተግባር በአባል ሀገራቱ ዘንድም እንዲስፋፋ ጥረታቸውን እንደሚያጠናክሩ ነው የገለጹት።
የግብርና ሚኒስትር ደኤታ ሳኒ ረዲ በበኩላቸው የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃግብር ለግብርና ዘርፍ ካለው ጠቀሜታ አንጻር እየተሠራ
ያለው ሥራ የሚደገፍ ነው ብለዋል።
ችግኝ የምግብ ፍላጎትን ከማሟላት ባለፈ የቤተሰብ የኀይል ፍላጎት ማሟያ ሆኖም የሚያገለግል በመሆኑ የተጀመረው ጥረት
ይጠናከራል ነው ያሉት።
በዚህ ዓመትም ኢትዮጵያ 6 ቢሊዬን ችግኝ በሀገር ውስጥ ለመትከል ማቀዷንና አንድ ቢሊዬን ደግሞ ለጎረቤት ሀገራት
ማዘጋጀቷን ጠቅሰዋል።
እቅዱ እንዲሳካ ወጣቶች የነገ ሕይወታቸው የተሻለ እንዲሆን ለዚህ በጎ ተግባር ሊረባረቡ እንደሚገባም ተናግረዋል።
የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኀይል አባል ሀገራት ወጣቶችም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ችግኝ በመትከላቸው ሊመሰገኑ ይግባል
ነው ያሉት።
የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ ህይወት ኀይሉ ችግኝ ተካላ የድንበር ተሻጋሪ በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል
መሆኑን ገልጸዋል።
እንዲህ አይነት ተግባር ጠቃሚና የጋራ ግንኙነትን ከማጠናከር ባሻገር ትስስርም የሚያበረታ በመሆኑ ሊለመድ ይገባል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ወጣቶችም በሌሎች የቀጣናው ሀገራት ተዘዋውረው ችግኝ መትከልና ለሌሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሰጡ
እቅድ መኖሩን ገልጸዋል።
ብሩንዳዊቷ ወጣት አይሚ ንሽሚርማናና ኬኒያዊው ወጣት አለን ሩቶ ”ወጣቶች ከምንም በላይ ለቀጣናው ሰላም መቆም
አለባቸው” ይላሉ። ይህ ሲሆን ለነገ ሕይወታቸው የተሻለ የሚያደርጉባቸው መንገዶች ላይ ማተኮር እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
ለዚህ ደግሞ የአካባቢ ጥበቃ ማድረግና ችግኝ መትከል የዘውተር ተግባር ቢሆን የተሻለ መሆኑን ይመክራሉ።
የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኀይል 10 ሀገራትን በአባልነት ይዟል፤ በሰላምና ደኅንነት ላይም አተኩሮ የሚሠራ ተቋም ነው። ኢዜአ
እንደዘገበው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleቡሩንዲ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ተጠቃሚ ለመሆን የታላቁ ህዳሴ ግድብን መጠናቀቅ እየጠበቀች መሆኑ ተገለጸ።
Next articleማን ነው አምባሳደር?