
የባሕር ዳር፡ መስከረም 11/2012 ዓ.ም (አብመድ) ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና ካሕናት በባሕር ዳር ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ በምዕመኗቹና በቤተ ክርስቲያኗ ላይ የሚፈፀመውን ግፍ እንዲቆም የሚጠይቅ ሠላማዊ ሠልፍ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በሰልፉ ላይ ‹‹በቤተ ክርስቲያንና በምዕመኖቿ ላይ የሚፈጸመው ግፍና መከራ ይቁም፡፡ በቤተ ክርስቲያንና ምዕመኖቿ ላይ ግፍ የፈጸሙት በሕግ ይጠየቁ፡፡›› የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው፡፡
ከባሕር ዳር የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በመነሳት ሰልፈኞቹ ወደ መስቀል አደባባይ እየተጓዙ መልዕክቶቻቸውን እያስተጋቡ ነው፡፡
ተመሣሣይ ዓላማ ያላቸው ሠልፎች በወልድያ፣ ፍኖተ ሠላም፣ ደባርቅ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደብረ ብርሃንና ሌሎችም ከተሞች እንደሚካሄዱ ታውቋል፡፡
ዝርዝር በሰልፉ ላይ የሚተላለፉ መልዕክቶችን እንደደረሱን የምናቀርብ ይሆናል፡፡
ፎቶ፡- ደጀኔ በቀለ እና ግርማ ተጫነ