የፌደሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ተግባር ለመዘርዘር ተሻሽሎ የወጣውን አዋጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸደቀ።

307
የፌደሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ተግባር ለመዘርዘር ተሻሽሎ የወጣውን አዋጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸደቀ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የፌደሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ተግባር ለመዘርዘር ተሻሽሎ የወጣውን አዋጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸደቀ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ ልዩ ስብሰባውን አካሂዷል።
በዚህም የፌደሬሽን ምክር ቤትን ስልጣንና ተግባርን ለመዘርዘር ተሻሽሎ የወጣውን አዋጅ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በዓለም አቀፉ የልማት ማህበርና በኢትዮጵያ መካከል ለተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲውል የተፈረሙ አራት የብድር ስምምነቶችን አጽድቋል።
ምክር ቤቱ በዛሬ ስብሰባው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ የመንገድ ደህንነት ቻርተርና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር የተስማማችባቸውን ሁለት የመንገድ ደህንነት ቻርተሮችንም ማጽደቁን ኢዜአ ዘግቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበመጠናቀቅ ሂደት ላይ የሚገኘው የጎርፍ ማፋሰሻ ዲች ግንባታ መፍረሱ ለጎርፍ አደጋ ስጋት ዳርጎናል ሲሉ በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንዳውሃ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
Next articleቡሩንዲ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ተጠቃሚ ለመሆን የታላቁ ህዳሴ ግድብን መጠናቀቅ እየጠበቀች መሆኑ ተገለጸ።