
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የልጆቿን ድጋፍ ይበልጥ የምትፈልግበት ወቅት በመሆኑ የሚደረገው ርብርብ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አምባሳደር ሙክታር ከድር ጥሪ አቀረቡ፡፡
ባሕር ዳር: ሰኔ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአውስትራሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በበይነ መረብ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ሙክታር ከድር በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አምባሳደሩ በተለይም በትግራይ ክልል መንግሥት ስለወሰደው ሰብዓዊ የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታና ከታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት ጋር ባለው ድርድር የኢትዮጵያን አቋም እንዲሁም ኢትዮጵያ በቅርቡ ያካሄደችውን 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ አብራርተዋል፡፡
አምባሳደሩ በዓመቱ የዳያስፖራ አባላቱ ላደረጉት የነቃ ተሳትፎና ለተገኙ ውጤቶች ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የልጆቿን ድጋፍ ይበልጥ የምትፈልግበት ወቅት በመሆኑ ርብርቡ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በውይይቱ ከተሳታፊዎች የተሰጡ ግብዓቶችን በመውሰድ በቀጣይ የበለጠ ውጤት ለማምጣት መስራት እንደሚገባ ከመግባባት ላይ ተደርሷል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ