የኢትዮጵያ መርከብ ከ20 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሶማሌ ላንድ በርበራ ወደብ መደበኛ የጭነት አገልግሎት መስጠት ጀመረች።

237
የኢትዮጵያ መርከብ ከ20 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሶማሌ ላንድ በርበራ ወደብ መደበኛ የጭነት አገልግሎት መስጠት ጀመረች።
ባሕር ዳር: ሰኔ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ንብረት የሆነችውና “ጊቤ” በሚል ስያሜ የምትታወቀው መርከብ ከ20 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሶማሌ ላንድ በርበራ ወደብ መደበኛ የጭነት አገልግሎት መስጠት መጀመሯን ድርጅቱ ገልጿል።
መርከቧ “ገልፍ ኢንዲያ ሰብ ኮንቲነንት” ከሚባለው አካባቢ 11 ሺህ 200 ቶን ስኳርና ሩዝ በመጫን በርበራ ወደብ አድርሳለች።
የበርበራ ተርሚናል ኮርደር የመጀመሪያ ዙር ማስፋፊያ ፕሮጀክት 500 ሺህ ኮንቴነሮችን መያዝ የሚችል ተርሚናል እንደሆነና በዓመት አንድ ሚሊዮን ኮንቴነሮችን ማስተናገድ እንደሚችል ከትራንስፖርት ሚኒስቴር የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሳ ቢሂ፣ የኢፌዴሪ ከፍተኛ ልዑካን እና የዲፒ ወርልድ ዳይሬክተር ሱልጣን ቢን ሱሌይማን በተገኙበት የበርበራ ወደብ የኮንቴነር ተርሚናል በይፋ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየፖለቲካ ፓርቲዎች በክልልና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ሊቆሙ እንደሚገባ ተገለጸ።
Next articleከ247 ሚሊዮን በላይ ችግኝ በአንድ ጀንበር ለመትከል መዘጋጀቱን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡