በደቡብ ሱዳን ቦር የሚገኘው የ14ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የተባበሩት መንግሥታትን የሰላም ማስከበር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆነ።

133

በደቡብ ሱዳን ቦር የሚገኘው የ14ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የተባበሩት መንግሥታትን የሰላም ማስከበር ሜዳልያ
ተሸላሚ ሆነ።
ባሕር ዳር: ሰኔ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ሱዳን የተሰማራው የሰላም አስከባሪ (ዩናሚስ) ምክትል ኮማንድ ሜጀር
ጀነራል ኤም ዲ ማይን ኡላህ ቾድሪ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ በግዳጅ አፈፃፀሙ ጠንካራ ፣ የሚሰጠውን
አስቸጋሪ ተልዕኮ በብቃት የሚወጣ ፣ በከፍተኛ ወታደራዊ ዲሲፒሊን የታነፀ ነው።
በደቡብ ሱዳን በተሰጠው ቀጣና አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ላደረገው ላቅ ያለ አበርክቶ የተባበሩት መንግሥታት የሰላም
ማስከበር ሜዳልያ በክብር ተሰጥቶታል ብለዋል።
በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነቢል ማህዲ አብዱላሂ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በተባበሩት
መንግሥታትም ኾነ በአፍሪካ ሕብረት በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ለረጅም ዓመታት አኩሪ ታሪክ ያላት ሀገር መሆኗን ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሠራዊት ሕዝባዊነት ያለው፣ በገባበት ኹሉ የሀገሩ አምባሳደር መሆኑን ገልጸዋል ።
በሜዳልያ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተባበሩት መንግሥታት የሥራ ኀላፊዎች፣ ወታደራዊ አታሼዎች የዩናሚስ ከፍተኛ
መኮንኖችንና የተለያዩ ሀገራት እንግዶች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበባሕር ዳር ሊከሰት የሚችለዉን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል የሚያስችል ሥራ መሥራቱን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለሥልጣን ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
Next articleየመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚያካሂደውን ስብሰባ በመቃወም ሰልፍ ሊካሄድ ነው።