በባሕር ዳር ሊከሰት የሚችለዉን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል የሚያስችል ሥራ መሥራቱን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለሥልጣን ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

120

በባሕር ዳር ሊከሰት የሚችለዉን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል የሚያስችል ሥራ መሥራቱን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ
ባለሥልጣን ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለሥልጣን ጽሕፈት ቤት ከመጋቢት 2013
ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ የሚገኙትን ዋና ዋና የጎርፍ ውኃ ማስወገጃ ቦዮችን የመጥረግ ሥራ መሠራቱን አስታውቋል።
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለሥልጣን ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አዳነ ጌታነህ ክረምት ገብቶ የጎርፍ መጥለቅለቅ
ከመከሰቱ በፊት የጎርፍ ማፋሰሻ ሥራ በ150 ባለሙያዎች ሲሠራ መቆየቱን አስረድተዋል።
ከዓባይ ወንዝ እስከ ጣና ሀይቅ 3 ነጥብ 8 ኪሎሜትር ያለው ዋና የጎርፍ ማስወገጃ ቦይ ጠረጋ ተደርጓል ብለዋል። ሥራውን
ለማከናወን ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበትም ገልጸዋል።
የጎርፍ መጥለቅለቅ ምክንያ የቦዮች በቆሻሻ መሞላት በመኾኑ ኅብረተሰቡ የተገነባለትን ማፋሰሻ በአግባቡ መያዝ እንዳለበትም
አቶ አዳነ አሳስበዋል።
“ኅብረተሰቡ በተገነባለት መንገድ አሸዋ ሲደፋ፣ ድንጋይ ሲከምር፣ እንጨት ሲፈልጥበት ይታያል” ያሉት ሥራ አስኪያጁ እነዚህ
ድርጊቶች የጎርፍ መጥለቅለቅ ምክንያት ስለኾኑ ጉዳት ከመምጣቱ በፊት ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ብለዋል። ጽሕፈት ቤታቸው
አሁን ላይ በግንባታ ምክንያት የተዘጉ ቦዮችን የመክፈትና ጎርፉ የተፈጥሮ ይዘቱን ጠብቆ እንዲወርድ የማስተንፈስ ሥራ
እየተከናወነ መኾኑንም አመላክቷል።
የባሕር ዳር የተፈጥሮ የመሬት አቀማመጥ ለጎርፍ ተጋላጭ እንደመኾኑ ወቅታቂ ሥራ ሳይኾን ዘላቂ መፍትሔ ያስፈልጋል ብለዋል።
በመኾኑም ከባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት እየሠሩ መኾኑን ጠቁመዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleለግብርና ግብዓት 7 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ መቅረቡን ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር አስታወቁ።
Next articleበደቡብ ሱዳን ቦር የሚገኘው የ14ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የተባበሩት መንግሥታትን የሰላም ማስከበር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆነ።