ለግብርና ግብዓት 7 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ መቅረቡን ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር አስታወቁ።

200

ለግብርና ግብዓት 7 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ መቅረቡን ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር አስታወቁ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት
መግለጫ ክልሉ በአሁኑ ወቅት መደበኛ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። ርእሰ
መስተዳድሩ “በክልሉ ሳይታረስ የሚከርም መሬት መኖር የለበትም ተብሎ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን
ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን እየተሠራ ነው” ብለዋል።
ለግብርና ግብዓት 7 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ መቅረቡንም አስታውቀዋል። የኩታ ገጠም አስተራረስን ውጤታማ በሆነ መንገድ
ለመፈጸም እየተሠራ ስለመሆኑም ተናግረዋል። የኩታ ገጠም እርሻ በአርሶ አደሮች ባሕል እየሆነ ሄዷልም ነው ያሉት። የበጋ
የመስኖ ስንዴ ጥሩ ተሞክሮ ተገኝቷል፣ በሚቀጥሉት ጊዜያትም ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል ።
በሌላ በኩል የአረንጓዴ አሻራ በክልሉ በአግባቡ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአማራ ክልል 2 ቢሊዮን ችግኝ እንደሚተከልም
አስታውቀዋል፡፡ በአረንጓዴ አሻራው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ላይ ትኩረት እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡
አረንጓዴ አሻራውን ከሥራ እድል ፈጠራ ጋር በማያያዝ እንደሚሠራም አስታውቀዋል፡፡
በክልሉ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ በትኩረት የሚሠራበት ጉዳይ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚታዩ የኢንቨስትመንት ማነቆዎች አፋጣኝ መፍትሔ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።
Next articleበባሕር ዳር ሊከሰት የሚችለዉን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል የሚያስችል ሥራ መሥራቱን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለሥልጣን ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።