በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚታዩ የኢንቨስትመንት ማነቆዎች አፋጣኝ መፍትሔ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።

173

በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚታዩ የኢንቨስትመንት ማነቆዎች አፋጣኝ መፍትሔ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ
ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።
ባሕር ዳር: ሰኔ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ የሚገኙ የውጭ ኢንቨስተሮች የሚያጋጥማቸውን ማነቆዎች ለመፍታት
የተቋቋመው ሀገራዊ የቅንጅት መድረክ መደበኛ ስብሰባ ተካሂዷል።
መድረኩን የመሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚታዩ
የኢንቨስትመንት ችግሮች አፋጣኝ መፍትሔ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በአጠቃላይ በዘርፉ የሚታዩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትም የተጠያቂነት ሥርዓትን እስከታች ድረስ በማውረድ ክትትል
ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የውጭ ቀጥተኛና ሌሎችም ኢንቨስትመንቶች ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮች ጥቅል ጉዳቱ በሀገር ላይ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ሁሉም
የሚመለከተው አካል ይህንን ተገንዝቦ ችግሩን የሚመጥን አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥ ነው ያሳሰቡት።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጽዮን ተክሉ በኢትዮጵያ መዋለ ነዋያቸውን ያፈሰሱ ባለሃብቶች ስለሀገሪቱ ምን ይላሉ በሚል ርዕሰ
ጉዳይ ላይ ገለፃ አቅርበዋል።
በሀገሪቱ ያለው የጸጥታ ሁኔታ የብዙ ኢንቨስተሮች ስጋት ቢሆንም የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ከሰላም
ሚኒስቴር፣ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽንና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተሠራ የተቀናጀ ሥራ ውጤታማ ተግባር ማከናወን ተችሏል
ነው ያሉት።
ኢንቨስትመንትን የማያበረታቱ የተለያዩ ተቋማዊ ችግሮች አሁንም የዘርፉ እድገት ማነቆ በመሆናቸው አፋጣኝ መፍትሔ
እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
የኢፌዲሪ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ በበኩላቸው ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ጋር ተያይዞ ከክልሎች ጋር
ያለው የቅንጅታዊ አሠራር ክፍተት ዘርፉን እየጎዳው ያለ ተግባር መሆኑን አንስተዋል።
ከጸጥታና መሬት አቅርቦት ጋር ያሉ ችግሮችም የዘርፉ ትልቁ ማነቆ መሆናቸውን ኮሚሽነር ሌሊሴ ጠቁመዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ
በዘርፉ ከዚህ ቀደም እንዲሻሻሉ ቅሬታ ከቀረበባቸው መስኮች በኃይል አቅርቦት ላይ ከፍተኛ መሻሻል መኖሩንም ተናግረዋል።
ከኃይል አቅርቦት ጋር በተያያዘ 36 ቅሬታዎች ቀርበው እንደነበር ያስታወሱት ኮሚሽነሯ በአሁን ጊዜ ጊዜም 31 ሙሉ ለሙሉ
መፍትሔ ሲያገኙ ሌሎች ቅሬዎችንም ለማስተካከል እየተሠራ መሆኑን ኮሚሽነሯ አስረድተዋል፡፡
በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ በበኩላቸው በኢንቨስትመንት ዘርፉ
ላይ የሚታየው የማስፈፀም ችግሮች ዘርፉን እየጎዳው መሆኑን ተናግረዋል። በሁሉም አካባቢዎች ያሉ የአስፈፃሚና ባለድርሻ
አካላት የዘርፉን ጥቅም በሚገባ በመረዳት ማነቆዎችን ፈተው አፋጣኝ ለውጥ ማምጣት እንደሚገባም ነው ያስገነዘቡት፡፡
የውጭ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በሚያደርጓቸው የኢንቨስትመንት እንቅስቅሴዎች ያጋጥሟቸውን ማነቆዎች የሚመለከታቸው
ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አሠራሩ በሚፈቅደው ልክ መፈታት እንዳለበትና ኢትዮጵያን ለባለሃብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት መዳረሻ
ማድረግ፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ችግሮች ዙሪያ የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ አስፈጻሚዎች የጋራ መድረክ በማዘጋጀት
መወያየት እንዲሁም ባለሀብቱ ከመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመደበኛነት ተገናኝቶ የሚወያይበትን መድረክ ማዘጋጀት
አስፈላጊ እንደሆነ አቅጣጫ ተቀምጧል።
በመድረኩም ከተለያዩ የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የተወከሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ከውጭ
ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ወጣቶች በሰላምና አካባቢ ጥበቃ በኢትዮጵያ የልምድ ልውውጥ እያደረጉ ነው።
Next articleለግብርና ግብዓት 7 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ መቅረቡን ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር አስታወቁ።