
የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ወጣቶች በሰላምና አካባቢ ጥበቃ በኢትዮጵያ የልምድ ልውውጥ እያደረጉ ነው።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ወጣቶች በሰላምና አካባቢ ጥበቃ የልምድ ልውውጥ
የሚያደርጉበት ሴሚናር በአዲሰ አበባ መጀመሩን የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ይፋ አድርገዋል።
በአዲስ አበባ የተጀመረው ከ10 የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ወጣቶች በሰላምና በአካባቢ ጥበቃ ላይ ያላቸውን
ተሳትፎ በሚያጎለብቱበትና ልምድ የሚለዋወጡበት ብሎም በሀገራቱ ላይ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በሚደረጉ ጥረቶች ሚናቸውን
እንዲወጡ የማስቻል ዓላማ ያለው ሴሚናር መሆኑ ተገልጿል።
አፍሪካ የወጣቶች አህጉር እንደመሆኗ መጠን ወጣቶች ሰላምን በመጠበቅና በመንከባከብ ብቻ ሳይሆን አዎንታዊ ሰላምን እንዴት
ማምጣት ይችላሉ የሚለውን ፀንሰ-ሐሳብ በጥልቀት እንዲመለከቱ ያግዛል ተብሏል።
የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀነራል ጌታቸው ሽፈራው በበኩላቸው ወጣቶች በቀጠናው ሰላምን
በማስፈንና በአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ላይ ተግባራዊ ተሳትፎ ለማድረግ የሚችሉበትን የጋራ ዓላማ አንግበው እንዲንቀሳቀሱ
የሚያስችል መድረክ መሆኑን አመልክተዋል።
ድንበርየለሽ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት መጀመርን ይፋ በማድረግ በእንጦጦ ፓርክ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም
እንደሚከናወን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m