የተፈናቀሉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም ሀብት የማሰባሰብና ቤታቸውን የመገንባት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡

155

የተፈናቀሉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም ሀብት የማሰባሰብና ቤታቸውን የመገንባት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የአማራ ክልል
ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸው
ከተመለከቱት ውስጥ አንዱ የተፈናቀሉ ወገኖችን ጉዳይ ነው፡፡
የአማራ ክልልን የተፈናቃዮች ጉዳይ ሲፈትነው እንደከረመ የተናገሩት ርእሰ መሥተዳድሩ ከክልሉ ውጭና በክልሉ ውስጥ
በሚፈጠሩ ግጭቶች ዜጎች መፈናቀላቸውንም አስታውሰዋል፡፡
የክልሉ መንግሥት በክልሉ ውስጥ ያለውን የመፈናቀል ችግር ለመፍታት ሥራዎች መሠራታቸውንም ገልጸዋል፡፡
በክልሉ ሰሜን ሸዋ ዞንና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የተከሰተውን ችግር ለመፍታት ከፍተኛ ሥራ መሠራቱንና አሁንም በመሠራት
ላይ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
አካባቢው ሰላም እንዲሆንና ተጨማሪ ችግር እንዳይከሰት፣ ሀብትና ንብረት የወደመባቸውን ወገኖች በዘላቂነት ለማቋቋም ሀብት
የማሰባሰብና ቤታቸውን የመገንባት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ተፈናቃይ ወገኖችን የሚደግፍ ክልላዊ ኮሚቴ ተደራጅቶ እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው የሚገኙ ወገኖችን ለመመለስ እየተሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ክልሉ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝና ከኦሮሚያ ክልል መንግሥታት ጋር እየሠራ መሆኑንና ውጤት መገኘቱንም አስታውቀዋል፡፡ ከኦሮሚያ
ክልል ጋር የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመመለስ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው የነበሩ ወገኖችን ወደ አካባቢያቸው የመመለስና በተደራጀ ሁኔታ እንዲኖሩ የሚያስችል ሥራ
መሠራቱን ነው ያስታወቁት፡፡ ተፈናቃይ ወገኖችን የመመለስ ሥራ መሠራቱንም አስታውቀዋል፡፡ ራሳቸውን ሊጠብቁ የሚችሉበትን
የማደራጀት ሥራ እየተሠራ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4

Previous article“ወልቃይት፣ ጠገዴንና ራያን በጉልበት ለመውሰድ የሚደረግ እንቅስቃሴ ካለ ማናቸውንም ዋጋ እንከፍላለን›› ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር
Next articleየምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት ወጣቶች በሰላምና አካባቢ ጥበቃ በኢትዮጵያ የልምድ ልውውጥ እያደረጉ ነው።