ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ደብዳቤ ለጸጥታው ምክር ቤት አስገባች፡፡

169
ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ደብዳቤ ለጸጥታው ምክር ቤት አስገባች፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአረብ ሊግ ሀገራት የጸጥታው ምክር ቤትና የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ጣልጋ እንዲገቡ ግፊት የሚያደርግ ጥያቄ በደብዳቤ አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትም ይሕንን በመቃወም ደብዳቤ ጽፏል፡፡
የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን ለጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በላኩት ደብዳቤ ሀገራቱ በተባበሩት መንግሥታት ሊታይ የማይገባን ጉዳይ በማንሳታቸው ኢትዮጵያ ደስተኛ አይደለችም ብለዋል፡፡
ግብጽ በዓባይ ጉዳይ ላይ ለምታራምደው አቋም አባል ሀገራቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ድጋፍ እየሰጡ መኾኑም በደብዳቤው ተብራርቷል፡፡ የሦስትዮሽ ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት በኩል እየተከናወነ መኾኑን ያስታወሰው ደብዳቤው የአረብ ሊግ ሀገራት የተከተሉት አካሄድ የአፍሪካ ሕብረትና የአረብ ሊግን ወንድማማችነትና የትብብር ግንኙነትን አደጋ ውስጥ የሚከት መኾኑን አመላክቷል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት ለኢትዮጵያ፣ ለሱዳን እና ለግብጽ የጋራ ተቋም መኾኑን በማንሳትም ሕብረቱ ‹‹ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ ›› በሚል መሪ ሀሳብ ሁሉንም አሸናፊ ሊያደርግ የሚችል የሶስትዮሽ መድረክ ማዘጋጀቱም ተነስቷል፡፡
በአፍሪካ ሕብረት መሪነት የሚካሄደውን የሦስትዮሽ ድርድር ኢትዮጵያ በደስታ ተቀብላ ሂደቱ ስኬታማ እንዲኾን በቁርጠኝነት እየሠራች መኾኑንም አመላክቷል፤ ሁለቱ ሀገራት ይህንኑ በቅን ልቦና ተቀብለው የድርድር ሂደቱን ማስቀጠል እንዳለባቸው ነው በደብዳቤው የተጠቀሰው፡፡
የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን የውኃ አጠቃቀም በተመለከተ ሁለቱ ሀገራት ዓለም አቀፍ ሕግ ተከትለው እንዲንቀሳቀሱ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማበረታታ አለበት ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ አቅርቧል፡፡ መረጃው የተገኘው ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበግብር ዘመኑ ከእቅዱ 85 በመቶ ገቢ መሰብሰቡን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ፡፡
Next article“ወልቃይት፣ ጠገዴንና ራያን በጉልበት ለመውሰድ የሚደረግ እንቅስቃሴ ካለ ማናቸውንም ዋጋ እንከፍላለን›› ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር