
የክብርት ዶክተር አበበች ጎበና አስክሬን ሽኝት መርኃግብር እየተከናወነ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የክብርት ዶክተር አበበች ጎበና አስክሬን አራዳ ክፍለ ከተማ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ጸሎተ ፍትሃትና የሽኝት ፕሮግራም እየተካሄደ ነው።
በመስቀል አደባባይም የስንብት ሥነ-ሥርዓት ተዘጋጅቷል፡፡ ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሥርዓተ ቀብራቸው ይፈፀማል መባሉን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና በበጎ እድራጎት ሥራቸው እውቅናን ያተረፉ፣ የአፍሪካዋ “ማዘር ትሬዛ” የሚል ስያሜን ያገኙ እና በልጆቻቸውም “እዳዬ” ተብለው ይጠራሉ።
ከ41 ዓመታት በላይ ወላጆቻቸውን በተለያዩ ምክንያቶች ያጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ልጆችን ተንከባክበውና አሳድገው ለቁም ነገር አብቅተዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ