የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ የክረምት በጎ አድራጎት መርኃግብርን አስጀመሩ፡፡

244
የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ የክረምት በጎ አድራጎት መርኃግብርን አስጀመሩ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአዲስ አበባ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የአቅመ ደካሞችን ቤቶች በማደስ በትምህርት ዘርፉ የሚካሄደውን የክረምት የበጎ አድራጎት መርኃግብርን በይፋ አስጀምረዋል።
በበጎ አድራጎት መርኃግብሩም በትምህርት ሚኒስቴር ድጋፍ በክፍለ ከተማው 15 የአቅመ ደካሞች ቤት እንደሚታደስም ተገልጿል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ.ር) የኢትዮጵያዊነት መገለጫ የሆነው የመተጋገዝ እና የመደጋገፍ ባህልን መሰረት በማድረግ የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ በመቻላችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል።
በሁለት ሳምንት ውስጥም ቤቶቹ ታድሰው ለነዋሪዎቹ እንደሚያስረክቡም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ለአቅመ ደካሞቹም ቤቱን ከማደስ ባሻገር አስፈላጊ የቤት እቃዎችም እንደሚሟሉ ተገልጿል።
ተማሪዎች በክረምቱ መርኃግብር በየአካባቢያቸው በተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች በመሳተፍ ከወገን አልፈው ሀገርን የማገዝ ኀላፊነታቸውን በንቃት እንዲወጡ ሚኒስትሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየኳታሩ ወተት እና የወተት ውጤቶች አምራች የሆነው ባላድና ኩባንያ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ለመሠማራት እንደሚፈልግ ገለጸ፡፡
Next articleየክብርት ዶክተር አበበች ጎበና አስክሬን ሽኝት መርኃግብር እየተከናወነ ነው፡፡