
የኳታሩ ወተት እና የወተት ውጤቶች አምራች የሆነው ባላድና ኩባንያ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ለመሠማራት እንደሚፈልግ ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በኳታር ቀዳሚ እና ግዙፍ የሆነው ባላድና ወተት እና የወተት ውጤቶች ማምረቻ ኩባንያ በእንስሳት እርባታ፣ በወተት እና የወተት ውጤቶች አመራረት፣ እንዲሁም የምርት አስተሻሸግ ሂደት ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች በኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ጉብኝት ተደርጓል፡፡
በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት በዚሁ ዘርፍ በኢንቨስትመንት ለመሠማራት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።
በጉብኝቱ ወቅትም በኢትዮጵያ ወተት እና የወተት ውጤቶችን ለማምረት አመቺ የኢንቨስትመንት ሁኔታ እንዳለ በዲፕሎማቶቹ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በኳታር እ.ኤ.አ በ 2017 በገልፍ ሀገሮች የተጣለውን ማዕቀብ ተከትሎ የሀገሪቱን የምግብ ፍጆታ በሀገር ውስጥ ለማምረት ወደ ሥራ የገባው ድርጅ በአሁኑ ወቅት ኳታር በወተት እና የወተት ውጤቶች ሙሉ በሙሉ ራሷን እንድትችል ማድረግ አስችሏል።
ባላድና በ2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ካሬ ሜትር መሬት ላይ በእንስሳት እርባታ እና በወተት ውጤቶች ማምረት የተሠማራ እና በዘርፉ ከፍተኛ እውቀት እና ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች እየተመራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበ በኳታር ብሎም በቀጣናው ቀዳሚ የሆነ ድርጅት መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ