የመከላከያ ሰራዊታችን ከህግ ማስከበር ዘመቻ ሲመለስ ባረፈበትና በየመስመሩ በተጓዘበት ህዝቡ ላደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ የመከላከያ ሚኒስቴር ምስጋናውን አቀረበ።

727

የመከላከያ ሰራዊታችን ከህግ ማስከበር ዘመቻ ሲመለስ ባረፈበትና በየመስመሩ በተጓዘበት ህዝቡ ላደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ
የመከላከያ ሚኒስቴር ምስጋናውን አቀረበ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 28/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሚኒስቴሩ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮለኔል ጌትነት አዳነ፣ ከራሳችን በፊት ሕዝባችንን
ስናስቀድም፤ ሕዝባችን ደግሞ ካለው ዕለታዊ ጉርሱ ቀንሶ ይሰጣል ብለዋል።
“ከምንም በላይ ክብርና ፍቅርን ለገለፃችሁልን ሁሉ ምስጋናችን ወደር የለውም ” ብለዋል።
“በተለይም ሰራዊታችን ፣ እንኳንም ለኢትዮጵያ ህዝብ ዋጋ ከፈልን ያስባለው፣ ጎዳና ላይ ፍራፍሬ ሸጣችሁ ሳንቲም ለማትረፍ
ወጥታችሁ ሰራዊታችንን ስታዩ መኪናው ላይ አራግፋችሁ የሰጣችሁ ፣ ያተረፋችሁት ፍቅር ነውና እናንተን ይዘን የማንወርደው
ቁልቁለት፤ የማንወጣው አቀበት ፣ የማንሻገረው ችግር እና የማናሸንፈው ጠላት አይኖርም” ብለዋል።
ኮለኔል ጌትነት “እኛ ከፊት እናንተን ስንጠብቅ ፤ እናንተ ጀርባችንን በመጠበቅ ኢትዮጵያን ሁሌም አሸናፊ እናደርጋታለን ” ሲሉ
ተናግረዋል።
ህዝቡ የስንቅ ፣ ትጥቅና የሰው ኃይል ምንጫችን ብቻ ሳይሆን የሞራልም ከፍታ በመሆኑ ምስጋናችን ከልብ ነው ማለታቸውን
ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበኩር ጋዜጣ ሰኔ 28/2013 ዕትም
Next articleየኳታሩ ወተት እና የወተት ውጤቶች አምራች የሆነው ባላድና ኩባንያ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ለመሠማራት እንደሚፈልግ ገለጸ፡፡