የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሠራዊት አባላት በግዳጅ ቀጠናቸው አካባቢ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሰብዓዊ ድጋፎችን አደረጉ።

204

የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሠራዊት አባላት በግዳጅ ቀጠናቸው አካባቢ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሰብዓዊ ድጋፎችን
አደረጉ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 28/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ሱዳን የሚገኘዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ ሰላም
አስከባሪ የኢትዮጵያ ሠራዊት የ3ኛ ባታሊዮን አባላት በግዳጅ ቀጠናቸው አካባቢ ለሚገኙ አቅመ ደካማ የኅብረተሰብ ክፍሎች
የተለያዩ የሰብዓዊ ድጋፎችን አድረገዋል።
አባላቱ ከዕለት ፍጆታቸው ላይ በመቀነሰ ከጁባ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኮርዌስት በምትባል መንደር
ለሚገኙ ለአቅመ ደካማ አረጋዊያን አካል ጉዳተኞች፣ ለሴቶች እና ለህፃናት ያዘጋጁትን ሩዝ፣ ቦሎቄ፣ ዘይት፣ ሰኳር፣ ፓስታ እንዲሁም
ብርድልብስ እና አንሶላ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የሻላቃው የህከምና ቡድንም ዓለም አቀፍ ወረርሸኝ የሆነው የኮሮናቫይረስ መንስኤ እና የመከላከያ መንገዶችን በማስተማር
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎችን እንዲሁም ሳኒታይዘሮችን አድለዋል፡፡
በድጋፍ አሰጣጥ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የሻለቃው ምክትል አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ጠይቅ ዘመን ድጋፉ ከአካባቢው
ማኀበረሰብ ተወካዮች ጋር በመነጋገር በችግር የተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ለማገዝ ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በቀጣይም የአከባቢውን ኅብረተሰብ በሚጠቅም ማናቸውም ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ ወዳጅነታችንን እና አጋርነታችንን አጠናክረን
እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
በተረጂዎች ስም ድጋፉን በመቀበል ንግግር ያደረጉት የኮርዌስት ቀበሌ አሰተዳዳር ጆን ሙጅሽ ማኩር በበኩላቸው የኢትዮጵያ
ሰላም አስከባሪ ኀይል አባላት ከዚህ ቀደምም መሰል ድጋፎችን ያደረጉላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
በ15ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ለተደረገላቸው ድጋፍ በማኅበረሰቡ ስም ያላቸውን አድናቆት እና ምስጋናም
አቅርበዋል፡፡
መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“ሁሉም ነገር የሚኖረው ሀገር ሰላም ሲሆን ነው” ወይዘሮ ባንቹ አይጠገብ
Next articleበኩር ጋዜጣ ሰኔ 28/2013 ዕትም