“ሁሉም ነገር የሚኖረው ሀገር ሰላም ሲሆን ነው” ወይዘሮ ባንቹ አይጠገብ

378
“ሁሉም ነገር የሚኖረው ሀገር ሰላም ሲሆን ነው” ወይዘሮ ባንቹ አይጠገብ
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 28/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 04 ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ ባንቹ አይጠገብ ልጃቸው ሀብታም ጌትሽ የልዩ ኀይል ፖሊስ እንድትሆን አብረው መጥተው ሲያስመዘግቡ ስለሁኔታው ጠየቅናቸው “ሁሉም ነገር የሚኖረው ሀገር ሰላም ሲሆን ነው፤ ሀገር ሰላም ሲሆን ልጅ ወልዶ መሣም ይቻላል ሀገር ሰላም ካልሆነ ሁሉም ከንቱ ነው” ነው ያሉን።
ወይዘሮ ባንቹ አይጠገብ ልጃቸው የልዩ ኀይል ፖሊስ ሆና እንድትመዘገብ በሙሉ ፍቃደኝነት ይዘው አምጥተው አስመዝግበዋል።
በተለይም ትህነግ ከዚህ በፊት ይሠራው የነበረው ግፍ አልበቃ ብሎት አሁንም እንደለመደው የአማራን ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ መንቀሳቀሱ እንዳበሳጫቸው እና እኔ ባልችል ልጄ የበኩሏን አስተዋጽኦ እንድታበረክት ስልካት በደስታ ነው ብለዋል።
ተመዝጋቢዋ ሀብታም ጌትሽ በበኩሏ ትምህርት ቤት ስማር ጀምሮ ፖሊስ እና ወታደር የመሆን ራዕይ ስለነበረኝ ምኞቴን ለማሳካት የአማራ ልዩ ኀይል ፖሊስ ለመሆን በመመዝገቤ ደስተኛ ነኝ በማለት ገልጻለች።
የክልላችንም ሆነ የሀገራችን ሰላም ለመጠበቅ የአማራ ልዩ ኀይል ፖሊስን እንዲቀላቀሉ ሀብታም ጌትሽ መልዕክት ማስተላለፏን የደብረ ማርቆስ ከተማ ፖሊስ ሚዲያ ክፍልን ጠቅሶ የዘገበው የአማራ ፓሊስ ኮሚሽን ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት መገንቢያ ቦታ ለማግኘት ለተደራጁ ማኅበራት የተገለጸው የካሣ ክፍያ የተሻሻለውን የካሣ አከፋፈል መመሪያ መሠረት ያደረገ መሆኑን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
Next articleየኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ሠራዊት አባላት በግዳጅ ቀጠናቸው አካባቢ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሰብዓዊ ድጋፎችን አደረጉ።