
አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ኤዲ ሮው ጋር ተወያዩ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 28/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በሱዳን የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ጋር ዛሬ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱም አምባሳደሩ ስለ ትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ፣ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና የኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር ጉዳይን በተመለከተ የኢትዮጵያን አቋም አስረድተዋል፡፡
ዳይሬክተሩ በበኩላቸው ስለተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው፣ በቀጣይ ከኤምባሲው ጋር ተቀራርበው ለመሥራት ዝግጁነታቸውን ማረጋገጣቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ