የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረበው የቴሌቪዥን ጣቢያ ስያሜ ለውጥ ጥያቄ በባለስልጣኑ ተቀባይነት አገኘ።

362
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረበው የቴሌቪዥን ጣቢያ ስያሜ ለውጥ ጥያቄ በባለስልጣኑ ተቀባይነት አገኘ።
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 28/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለስልጣን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያቀረበለትን የቴሌቪዥን ጣቢያ ስያሜ ቅያሬ ጥያቄ ተቀበለ።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ‘ትግራይ ቴሌቪዥን’ በሚል ስያሜ የሚታወቀው ጣቢያ ‘ይሓ ቲቪ’ የሚል ስያሜ እንዲሰጠው ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት እንዳገኘ ባለስልጣኑ ለኢዜአ ገልጿል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ለኢዜአ እንዳረጋገጠው የስያሜ ጥያቄው ምላሽ ማግኘቱን ተከትሎ ጣቢያው በቅርብ ቀናት ውስጥ የአየር ስርጭት ይጀምራል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ኢትዮጵያን ማሸነፍ አይቻልም፤ ለብዙ ኃይሎች ይህን ቆም ብሎ ማሰብ ያስፈልጋል›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
Next articleበኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን ብሔራዊ የደኅንነት ስጋት ለመመከት የሚጠበቅበትን ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ገለጸ፡፡