የጎብኚ መዳረሻ የሆኑ አካባቢዎችን በማስተዋወቅ ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡

100
የጎብኚ መዳረሻ የሆኑ አካባቢዎችን በማስተዋወቅ ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 28/2013 ዓ.ም (አሚኮ)5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ በቱሪዝም ትልቅ አቅም ያላት ሀገር ናት ብለዋል፡፡ ብዙ ሥራ መሥራት ይገባናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅርሶችን መጠገን፣ አዳዲስ መዳረሻዎችን ማስፋትና ዓለም በሚገባ እንዲያውቀው ማድረግ እንደሚገባ ነው የተናሩት፡፡
ያልታወቁ አካባቢዎችን በማሳዎቅ ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቅርስ፣ ታሪክና ተፈጥሮ በቀላሉ የሚገኝ አለመሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ለቱሪዝም ዘርፍ ትኩረት በመስጠት ሰፋፊ ሥራዎች መጀመራቸውንም አስታውቀዋል፡፡
“በኢትዮጵያ ተዓምራዊ ቅርስ ነው ያለው፡፡ ማሳያት ከቻልን ብዙ ነገር ነው የሚያመጣው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ ለዚህም በትኩረት መሥራት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“የኢትዮጵያ የውጭ እዳ ጫና በጠቅላላ ዓመታዊ እድገት አንፃር ሲታይ ከነበረበት 37 በመቶ ወደ 26 በመቶ ገደማ ወርዷል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
Next articleየውጪ ኢንቨስትመንትን 20 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡