
በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ሳያቋርጡ እያከናወኑ እንደሚገኝ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በማኅበራዊ የትስስር ገጹ እንዳመላከተው በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ሳያቋርጡ እያከናወኑ እንደሆነ ሚኒስቴሩ ትግራይ ከሚገኙ ዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር ባደረገው ክትትል አረጋግጧል።
የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎችም ቦታው ድረስ በመገኘት የተማሪዎችን ድምጽ በመቅረጽ ለተማሪ ቤተሰብና ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ማሰማታቸውን በመግለጽ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እየሰጠ ያለውን መረጃ በተጨባጭ ማስረጃ በማረጋገጣቸው ምስጋናውን አቅርቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ