
“የኢትዮጵያ የርህራሄ ተምሳሌት የነበሩት አበበች ጎበናን ህልፈተ ህይወት ስሰማ እጅግ አዝኛለሁ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ህልፈተ ህይወት አስመልክቶ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም “የኢትዮጵያ የርህራሄ ተምሳሌት የነበሩት አበበች ጎበናን ህልፈተ ህይወት ስሰማ እጅግ አዝኛለሁ” ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ቤተሰቦች፣ ወዳጆቻቸው እና በሕይወታቸው ላይ ተጽዕኖ ለነበራቸው ሁሉ ከልብ መፅናናትን እመኛለሁ ነው ያሉት፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ