የተናጠል ተኩስ አቁም እና የመከላከያን ከመቀሌ መውጣት ተከትሎ የሕወሓት የሽብር ቡድን በመቀሌ እና በሌሎች የትግራይ ከተሞች በነዋሪዎች ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን እያደረሰ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

221
የተናጠል ተኩስ አቁም እና የመከላከያን ከመቀሌ መውጣት ተከትሎ የሕወሓት የሽብር ቡድን በመቀሌ እና በሌሎች የትግራይ ከተሞች በነዋሪዎች ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን እያደረሰ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የተናጠል ተኩስ አቁም እና የመከላከያን ከመቀሌ መውጣት ተከትሎ የሕወሓት የሽብር ቡድን በመቀሌ እና በሌሎች የትግራይ ከተሞች በመግባት በክልሉ ነዋሪ ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን እያደረሰ እንደሚገኝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡
በመቀሌ እና በሌሎች ከተሞች ከጊዜያዊ አስተዳደሩ እና ከመከላከያ ጋር ተባብራችኋል ያላቸውን ንጹሐን ላይ ግድያ እየፈጸመ ይገኛል ያለው የመረጃ ማጣሪያው ይህንም ተግባሩ በትግራይ ያለውን የሰብዓዊ አቅርቦቶች እጥረት አባብሶ በክልሉ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ እንዲፈጠር የሚያደርግ ነው ብሏል፡፡
በተጨማሪም የሽብር ቡድኑ መንግሥት ያደረገውን አይነት የተኩስ አቁም ከማድረግ ይልቅ የኢትዮጵያን እና የዓለምአቀፉን ማኅበረሰብ በሐሰተኛ ፕሮፓጋንዳዎቹ ለማታለል እና ትኩረት ለማግኘት በሚያደርገው መፍጨርጨር የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጪዎችንና የዜጎች ደኅንነት በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እያስገባ እንደሆነ ኢትዮጵያዊያን እና የዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ሊረዳ እንደሚገባም አስገንዝቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበበጎ ሥራቸው የሚታወቁት ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
Next article“ፖሊስነት ለሕዝብና ለሀገር ጥቅምና ክብር ሲባል ራስን አሳልፎ በመስጠት መስዋእትነት የሚከፈልበት ክቡር ሙያ ነው”