በበጎ ሥራቸው የሚታወቁት ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

1529

በበጎ ሥራቸው የሚታወቁት ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆች በማሳደግ በጎ ሥራቸው የሚታወቁት
ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና በ85 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
አበበች ጐበና ህፃናት ክብካቤና ልማት ማህበር መስራች የሆኑት ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና (እዳዬ) በ1972 ዓ.ም
ለመንፈሳዊ ጉዞ በሄዱበት በወቅቱ ተከስቶ በነበረው ድርቅ ሳቢያ ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ሁለት ህፃናትን በመያዝ ነበር የበጎ
አድራጎት ስራቸውን የጀመሩት።
የአፍሪዊቷ ማዘር ትሬዛ በሚል ስም የሚታወቁት የበርካቶች እናት ክብርት ዶክተር አበበች ባለፉት 41 ዓመታት በሺዎች
የሚቆጠሩ ህፃናትን ተንከባከበው ለቁምነገር ያበቁ ሲሆን በተለያዩ የድህነት ቅነሳ ፕሮግራሞችም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ
ለሚሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ መስጠታቸውን ከማኅበራቸው የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
ክብርት ዶክተር አበበች በተለያዩ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ መድረኮች ታላላቅ ሽልማቶችና እውቅናዎችን እንዲሁም ከጅማ
ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በሰብዓዊነት አገልግሎታቸው አግኝተዋል።
ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና በቅርቡ በኮሮና በሽታ ምክንያት በጳውሎስ ሆሰፒታል በጽኑ ህሙማን ክፍል ሲረዱ ቆይተው ዛሬ
ጠዋት በተወለዱ በ85 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ኢብኮ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበእንሰሳት ጤና አገልግሎት የግል ዘርፉን ተሳትፎ በማሳደግ ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠትና መንግሥት የአገልግሎት አሰጣጥ ቁጥጥርና ጥራትን ማስጠበቅ ላይ አተኩሮ እንዲሠራ የሚያስችል መመሪያ እየተዘጋጀ ነው፡፡
Next articleየተናጠል ተኩስ አቁም እና የመከላከያን ከመቀሌ መውጣት ተከትሎ የሕወሓት የሽብር ቡድን በመቀሌ እና በሌሎች የትግራይ ከተሞች በነዋሪዎች ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን እያደረሰ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡