በእንሰሳት ጤና አገልግሎት የግል ዘርፉን ተሳትፎ በማሳደግ ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠትና መንግሥት የአገልግሎት አሰጣጥ ቁጥጥርና ጥራትን ማስጠበቅ ላይ አተኩሮ እንዲሠራ የሚያስችል መመሪያ እየተዘጋጀ ነው፡፡

209

በእንሰሳት ጤና አገልግሎት የግል ዘርፉን ተሳትፎ በማሳደግ ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠትና መንግሥት የአገልግሎት
አሰጣጥ ቁጥጥርና ጥራትን ማስጠበቅ ላይ አተኩሮ እንዲሠራ የሚያስችል መመሪያ እየተዘጋጀ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የእንሰሳት ጤና አገልግሎት መመሪያ ሰነድ የመንግሥት፣ የግሉ ዘርፍ እና የተለያዩ
አካላትን በማሳተፍ እየተዘጋጀ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ግብርና ሚኒስቴር የእንሰሳት ጤና አገልግሎት በመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ማከናወን የሚያስችለዉን መመሪያ እያዘጋጀ
መሆኑን ገልጿል፡፡ በሰነዱ ላይ ከግብርና ሚኒስቴር፣ የተለያዩ ተቋማትና ክልሎች ከተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ዉይይት
ተካሂዷል።
ግብርና ሚኒስቴር በሚቀጥሉት አስር ዓመታት መሰረታዊ ለዉጥ ለማምጣት ከሚሠራባቸው ዘርፎች ውስጥ የእንሰሳት ጤና
አገልግሎት አንዱ ነው ተብሏል፡፡
ባለፉት ዓመታት አገልግሎቱ በመንግሥት ብቻውን ሲሠራ መቆየቱ ከተደራሽነት አኳያ መሻሻሎች ቢኖሩም ውጤታማነቱ ላይ ሰፊ
ዉስንነቶች መኖሩም ተጠቅሷል፡፡ በዚህም በሚቀጥሉት ዓመታት በአገልግሎቱ ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ በማሳደግ ዉጤታማ
አገልግሎት ለመስጠት እና መንግሥት የአገልግሎት አሰጣጥ ቁጥጥርና ጥራትን ማስጠበቅ ላይ አተኩሮ እንዲሠራ የሚያስችል
መመሪያ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ ግብርና ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አመላክቷል፡፡
መመሪያዉ ከእንሰሳት ጤና አገልግሎት አኳያ በሀገሪቱ ለመጀመርያ ጊዜ እየተዘጋጀ ያለ መሆኑ ተጠቅሟል፡፡ በመንግሥትና የግሉ
ዘርፍ አጋርነት የሚሰጡ የእንሰሳት ጤና አገልግሎት ምንነት እና የአፈፃፀም ሂደቶች፣ የመንግሥት፣ የግሉ ዘርፍ እና የተለያዩ
አካላት የሥራ ድርሻ በመለየት እና የአፈፃፀም ወሰኖችን የያዘ ነው፡፡
የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ዶክተር ዮሐንስ ግርማ የእንሰሳት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እና
ሀገሪቱን ከእንሰሳት ዘርፉ ማግኘት ያለባትን ጥቅም ለመጨመር የእንሰሳት ጤና አገልግሎት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የእንስሳት ጤና አገልግሎቱን ውጤታማ ለማድረግ የግል ዘርፉን በስፋት ለማሳተፍ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። የተዘጋጀዉ
መመሪያ በዘርፉ የሚሰጠዉን አገልግሎት በጥራት እና ተደራሽነት መሰረታዊ ለዉጥ ለማምጣት መሰረት የሚጥል እንደሆነም
አመላክተዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በተያዘለት ዕቅድ መሠረት እየተከናወነ ነው” ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ
Next articleበበጎ ሥራቸው የሚታወቁት ክብርት ዶክተር አበበች ጎበና ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡