
“የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በተያዘለት ዕቅድ መሠረት እየተከናወነ ነው” ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 27/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በተያዘለት እቅድና ፕሮግራም መሠረት
እየተከናወነ መሆኑን የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለጹ።
የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የቦርድ አባላት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኀይል ጋር በመሆን የህዳሴው ግድብ ግንባታ የደረሰበትን
ሁኔታ ትናንት በቦታው ተመልክተዋል።
በዚህም ወቅት የግድቡ ግንባታ በተያዘለት ዕቅድ መሠረት እየተከናወነ መሆኑን ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ ገልጸዋል።
በግድቡ ግንባታ ሂደት ለሚሳተፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች፣ የግንባታ አማካሪዎች እና በግድቡ ዙሪያ ድጋፍ ለሚያደርጉ ሁሉ
ምስጋና ማቅረባቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m