የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በሰኬት እንዲከናወን መከላከያ ሠራዊት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ፡፡

346

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በሰኬት እንዲከናወን መከላከያ ሠራዊት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል አስራት ዴኔሮ በቀጣናው
ተልዕኳቸውን እየተወጡ ከሚገኙ የሠራዊት አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ እንደተናገሩት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በትኩረት
የሚከታተለውን የግድቡን ግንባታ በየደረጃው ባሉ አመራርና የሠራዊቱ አባላት ሌት ተቀን አስተማማኝ ጥበቃና ክትትል በማድረግ
ግንባታው ያለምንም እንቅፋት በታቀደለት መሠረት እየተፋጠነ ይገኛል።
የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በሰኬት እንዲከናወን በቀጣናው የሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት እንደከዚህ ቀደሙ
ሁሉ በማንኛውም ሰዓት በየትኛውም ቦታ ሠራዊቱ በአስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝም አረጋግጠዋል፡፡
ሠራዊቱ በከፈለው መስዋዕትነት የመተከል ዞን ሰላም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ በመምጣቱ በዞኑ አምስት ወረዳዎች ሞትና
መፈናቀልን ማስቆም ተችሏል ነው ያሉት፡፡ ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎችን በየወረዳቸው የተመረጡ ስፍራዎች የመመለስ ሥራ በስኬት
ስለመከናወኑም ተናግረዋል።
በቀጣይም የዞኑን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ የተጀመረውን ተልዕኮ በማጠናከር የሠራዊት አባላት ግዳጃቸውን በላቀ ብቃት
መፈፀም እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡
በመተከል ዞን የመጣው ለውጥ የሠራዊቱና የሕዝቡ ድምር ውጤት ነው ያሉት ሌተናል ጄነራሉ የተገኘውን ድል ማስቀጠል
እንደሚገባ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበአዲስ አበባ ከተማ የአማራ ወጣቶች ማኅበር በአጣዬ እና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ፡፡
Next article“የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በተያዘለት ዕቅድ መሠረት እየተከናወነ ነው” ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ