
“በተመረቅንበት የሙያ መስክ ሕዝባችንን ለማገልገል ቁርጠኞች ነን” ተመራቂ ተማሪዎች
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 26/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ የሚገኘው ሀበሻ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ
ዘርፎች ሲያሰለጥናቸው የነበሩ ተማሪዎችን አስመርቋል።
ተማሪ ሀብታሙ አንለይ በኮሌጁ በነርሲንግ ዲፓርትመንት ተመራቂ ነው። ከኮሌጁ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት
በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል። በኮሌጁ በቆየባቸው የትምህርት ዓመታት ተግቶ በማጥናቱና ጊዜውን በአግባቡ
በመጠቀሙ ለከፍተኛ ውጤት መብቃቱን ተናግሯል።
የተማረበት የሙያ መስክ የሰው ልጅ ህይወትን የመታደግ ኃላፊነት መሆኑን የገለጸው ተማሪ ሀብታሙ በገባው ቃል መሠረት
ሕዝብን ለማገልገል ቁረጠኛ መሆኑን ተናግሯል::
ውጤታማ ለመሆን ፍላጎትና ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የገለጸችው ደግሞ በኮልጁ ከተመራቂ ሴት ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ
ውጤት በማምጣት ተሸላሚ የሆነችው የአካውንቲንግ የትምህርት ዘርፍ ተመራቂዋ ጥሩ መሃሪ ናት።
ከዚህ በኋላም በተመረቀችበት የሙያ መስክ በመሠማራት ለማገልገል ቁርጠኛ መሆኗን ነው የተናገረችው
መንግሥት ለግል ዘርፉ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሥራ በመግባት ኮሌጁ የ3ኛ ዙር
ተማሪዎችን ማስመረቁን የገለጹት ደግም የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አባተ ናቸው።
ባለፈው አንድ ዓመት ተኩል በሀገሪቱ የተከሰተውን የኮሮና ወረርሺች በመቋቋም ተማሪዎች ለምረቃ መብቃታቸውንም ጠቅሰዋል።
ኮሌጁ በዕውቀትና ክህሎት የዳበረ፣ የተማረ ዜጋ ለማፍራት በትኩረት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
በዛሬው የ3ኛ ዙር ምረቃ መርሃ ግብር በ5 የስልጠና ዘርፎች 602 ተማሪዎች መመረቃቸውን አስታውቀዋል። ተመራቂዎች
በኮሌጁ ያገኙትን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር ሥራ ፈላጊ ሳይሆን ሥራ ፈጣሪ በመሆን ሀገራቸውን ማገልገል እንዳከባቸው
መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ:– ዘመኑ ይርጋ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m