“ሠራዊቱ ለሕዝቡ የሚሰስተው ነገር የለም” ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ

271

“ሠራዊቱ ለሕዝቡ የሚሰስተው ነገር የለም” ሌተናል ጄኔራል ባጫ ደበሌ
ባሕር ዳር: ሰኔ 26/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሜጀር ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን
ተማሪዎች ዛሬ ባስመረቀበት ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የመከላከያ ሠራዊት የግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል
ባጫ ደበሌ “ሠራዊቱ ለሕዝቡ የሚሰስተው ነገር የለም” ብለዋል።
ተመራቂዎችም በሚሠማሩበት ሥራ የሠራዊቱን ዕሴት ተላብሰው ታሪካዊ ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለመላው የሀገሪቱ ሕዝቦች የሚያገለግል እንጂ ለአንድ ወገን የቆመ አለመሆኑንም ገልጸዋል።
ኮሌጁ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች 265 ተማሪዎችን አሰልጥኖ ዛሬ አስመርቋል።
ከተመራቂ ተማሪዎች ውስጥ 31 ሴቶች ናቸው፤ 12ቱ ደግሞ የሶማሊላንድ ወታደሮች መሆናቸው ተገልጿል።
ኮሌጁ ከጀርመን ኤምባሲ ጋር በመተባበር የገነባቸውን የማስፋፊያ ወርክሾፖችም ጉብኝት ተካሂዷል።
በዝግጅቱ ላይ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ፣ የተለያዩ ሀገራት አታሼዎች ፣ የሆለታ ከተማ ከንቲባና የተመራቂ ቤተሰቦች
መገኘታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለዜጎች ክብር ያለው አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባቸዋል” ሰላም ሚኒስቴር
Next article“በተመረቅንበት የሙያ መስክ ሕዝባችንን ለማገልገል ቁርጠኞች ነን” ተመራቂ ተማሪዎች